Hello, ሁል ጊዜ ሳስበው ግርም የሚለኝን ነገር ላጋራቹ እድሜ 18-22 ውስጥ ነኝ ብዙና የተለያዩ ስራዎችን ሰራለው በቀን 10K ETB እንዲሁም ከ100K በላም ምናምን በወር ምሰራበት አጋጣሚዎችም አሉ (#ቁጥሩቋሚባይሆንም) ያው ገንዘብ ደስታን ሙሉ ለሙሉ ይገዛል ብዬ ባላምንም ነገር ግን አንዳንዴ ምንም ደስታ አይሰማኝም ማለት ምን ሆኜ እንደሆነ ሁላ እንኳ ግራ እስክጋባ ድረስ!?😭 (ተዝናና ምናምን እንዳትሉኝ ያው በመጠኑም ቢሆን ስለምዝናና; ስራ መስራት በጣም ነው የሚያስደስተኝ ለተወሰነ ቀናት ምንም ካልሰራው በቃ መጨለል ነው የሚቀረኝ😫) እና እስቲ ደስተኛ እንድሆን ምን ማድረግ አለብኝ ትላላቹ?
Nov 17, 2021ወዳጄ ገንዘብ የደስታ ምክንያት ሚሆነው ስትሰጥ ብቻ ነው ያ ካልሆነ ግን ሺ ብትዝናና ምንም ደስተኛ ላትሆን ትችላለህ ነገር ግን ባንተ ምክንያት አንድ ሰው ሲደሰት ካየህ ግን ሁሌም ደሰተኛ ትሆናለህ።ሲለዚህ ከገንዘብህ ለተቸገረ:ለታመመ ሰው የቅምህን ለግስ ያን ፈጣሪ ደስታን ይለገስሀል።
Nov 17, 2021