ሰላም ሰዎችዬ✌️አንድ ምክር እንድትለግሱኝ ፈልጌ ነበረ.... ራስን ስለማጥፋት ማሰብ ከጀመርኩ 8 አመት ሆነኝ እናም ላለማድረግ ሁሉ እታገላለሁ አሁን ግን ስሜቴን መቆጣጠር ሁሉ አልቻልኩም ንዴት እና ጭንቀት እንዲሁ ፍርሃት ውስጤ ይመላለሳል እና ለጭንቀቴ መድሃኒት ልወስድ ፈለኩኝ ...ይህን ያሰብኩበት ምክንያት ስላቃተኝ ነው መንቃት ፣ፀሃይ ማየት፣ሰው ካጠገቤ ማግኘት ፣ስራ መስራት፣ትምህርት መማር፣መብላት ፣መጠጣት፣ራሴን ለማዳን መጣጣር፣ ችግርን ለሰው ማውራት ደከመኝ በቃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ...ስለዚህ መድሃኒት መቃም ለእኔ ቀለለኝ እናንተስ ምንትላላችሁ???
Nov 17, 2021ቆይ ራስህን አጥፍህ ከዛ ምን ሚከሰት መሰለህ እፎይታ አታስበው የማያልቅ መከራ ውስጥ ራስህን ትሰዳለህ ይልቅ ይሄን የሰይጣን ሀሳብ ማሰቡን አቁምና ወደ ቤተ እምነት ሂድ አለም የማይሰጥህን ሰላም እና እረፍት ታገኝበታለህ ጥዋት ማታ ጸሎት አርግ ጭንቀትህን ለአምላክህ አዋየው ይሰማሀል ያሳርፍሀል ተጠመቅ መንፈስህ ይታደሳል ሐሴትም ማድረግ ትጀምራለህ ከዛ የመኖር ትርጉም ይገባሃል አይዞህ...
Nov 17, 2021