ሰላም ቤተሰብ። ቤተክርስቲያን ውስጥ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" እና "በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ " አስራ ሁለት ጊዜ በሉ ሲባል አባቶች በቂ ጊዜ የማይሰጡት ለምንድን ነው? እነሱ በምን ፍጥነት ነው የሚሉት?
Nov 13, 202112ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ የምንልበት ምክንያት እግዚአብሔር ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለው ይላል እናም ስለ ስሙ ቁጣውን የሚያዘገይን አምላክ ስለ ስምክ ብቻ ሳይሆን ስለ ስምክ ስለ እያንዳንዱዋ ፊደል ስትል በቀን ባሉት 12ሰዓት በለሊት ባሉት 12 ሰዓት ውስጥ የሰራነውን ኃጢያት ማረን ይቅር በለን እያልን እንደሆነ ልብ ይሏል። አብ ወልድ መንፈስቅዱስ (12 ፊደል ) የዳዊት ልጅ ማረኝ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ ብሎ ከደዌው እንደዳነ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ እንድንድን የኃጢያት ስርየትን እንድናገኝ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን።በመሆኑም ይክን በምንልበት ግዜ በልማድ በጣም ባንፈጥን መልካም ነው። ማረን ስንል የሰራነውን ኃጢያት በማሰብ በተሰበረ ልቦና በተሰቀለ ሕሊና ማለቱ ተገቢ ነው።ከመስዋዕት ይልቅ የተሰበረ ልብን ለሚሻ አምላክ በተሰበረ ልባችን እንጂ በአንደበታችን ልማድ ብቻ ወሯሯጥ ከእግዚአብሔር አያገናኘንም ምንም እንኳን በካህኑ ስልጣን ኃጢያት ቢስተሰረይም። #ኃጢያትን ማሰብ የተቀበለውን ሕማማተ መስቀል ማሰብ ቁልፉ ነው።
Nov 14, 2021