ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ንስሃ መግባት እፈልጋለሁ ነገር ግን ሀጢያት ውስጥ የዘፈቀኝ ከባድ መንፈስ ንስሃ ብገባም ወደ ቀደመው ሀጢያቴ እንደሚመልሰኝ ይሰማኛል። ስለዚህ እኔ ያሰብኩት በመጀመርያ በጥምቀት ከዚህ ነገር ከተፈወስኩ በኋላ ንስሃ መግባት ነበር። ንስሃ ሳልገባ ጸበል ብገባ መርከስ አይሆንብኝም?
Nov 12, 2021ሁለቱን አንድ ላይ ማስኬድ ትችላለህ ወንድሜ ንስሐውን እና ጸበሉን...ደሞ ዋናው ነገር ያንተ ህልና ነው ህልናህን በመጸጸት ውስጥ ምላው ምን ያክል አምላክህን እንደበደልከው አስብ ከዛ እመነኝ ዳግመኛ ወደዛኛው ሀጥያት አትመለስም አይዞህ ፈጣሪ ይርዳህ🙏
Nov 13, 2021