Hello guys endet nachu my question is 12gna kifl temari negn ena betam yechenekegn yet University limret new ene software engineering new memar mifeligw ena yet gibi best new lesu enam Astu bigeba lifu minimeslal yikebdal wayis endet ne please info situgn
Nov 12, 2021ካፒቴን ኢትዮጵያ እባላለሁ የድሮ የመቐለ የአሁኑ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሲሆን ምክረን እንደሚቀጥለው አስቀምጣለሁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መሠረት በማድረግ እንድትሞሉ ምክረ ነው ✅የምትማሩት ትምህርት የሚኖርበት ✅የምትማሩትን ትምህርት በብዛት ተቀብሎ የሚያስተምር ✅በሰው ተገፋፍታችሁ የማትፈልጉትን በፍፁም እንዳትሞሉ! ስለራሳችሁ ከእናንተ በላይ የሚያውቅ የለምና❌ ✅የቤተሰብን አቅም በሚመጥብን(ያው የግቢ ገቢም ወጪ ስለሆነ💵) ✅የአከባቢ አየሩ ለጤናችሁ ምቹ መሆኑን ማወቅ(ለነገሩ ነው) ✅የአከባቢው አኗኗር ዘይቤ ከነ ኑሮ ውድነት(መቐለ ስማር ባንክ ሄጄ ብር እንዳወጣሁ ከባንኩ በር ነው ብሩ የሚያልቅብኝ) ✅የመጨረሻው አንድኛ እና ሁለተኛ ምክሮች ከምንም በላይ አክብሩ! ✅የዘንድሮውን ባላውቅም እኛ ጊዜ ውጤት ከታወቀ በኋላ ምርጫ የሚደረግ ከሆነ 🤜ውጤታችሁን በማየት ከፍተኛ ከሆነ የትም ሙሉ ምክኒያቱም (You are VIP) 500+ 🤜መካከለኛ ከሆነ ከአዲስ አበባ ውጭ ይደርሳችኋል ብየ አስባለሁ (400-500) 🤜ከ400 በታች 2ኛ ትውልድ በሙሉ ቅድሚያ ይሰጣችኋል ለምሳሌ ሚዛን-ቴፒ ፣አምቦ፣ወልቂጤ..... 🤜ማለፊያ አካባቢ በጠም አስቸጋሪ ይሆናል እንደት ብትሉኝ የማትፈልጉት ሊደርሳችሁ ስለሚችል ስለዚህ መፍትሄውን ልንገራችሁ 📌ብዙ የማይሞላው ትንሽም ቢሆን ፍላጎት ያላችሁን መማር የምትፈልጉት ትምህርት ያለበት! ✅ከሰማኋቸው በየዲፓርትመንት ጥሩ የሚባሉ 🤜ለሜዲስን እና ጤና ጎንደር 🤜ለኤሌክትሪካል እንጂኔሪንግ ሃዋሳ ፣ሚዛን ቴፒ፣መቐለ 🤜ለሃይድሮሊክስ አርባ ምንጭ 🤜ለአፕላይድ ባህር ዳር 🤜ለLAW ሚዛን ቴፒ #የማውቀው_ይሄን_ነው ➡️መልካም እድል! For more information join our channel 💚@Freshstudents💚 💛@Freshstudents💛 ❤️@Freshstudents❤️
Nov 12, 2021