አንድ ልጅ አለች እናም ማውራት ከጀመርን 3 ሳምንት ሊያልፈን ነው በጣም ተመችታኛለች እና ዛሬ እያወራን እያለ ድንገት ወደ ሽንት ቤት ስልኬን አስቀምጬ ሄድኩ እናም ጓደኛዬ አንስቶ የማይሆን ነገር ጻፈ አውቃለሁ የእሱ ነው ስህተቱ ግን እሱን ላስቀይመው አልፈለኩም ብናደድበትም። ስልክ ደውዬ ፈታ ለማድረግ ሞከርኩ ግን ተናዳለች ለማረጋጋት ብሞክርም አልሆነልኝም። ብሎክ አላደረገችኝም እና ሰው ደግሞ ዝም ሲለኝ ለኔ ትልቅ ቅጣት ነው የሞትኩ ነው የሚመስለኝ እስቲ ከእርሷ ጋር ጓደኝነቴን ለማደስ ምን እንዳደርግ ትመክሩኛላችሁ😞?
Nov 10, 2021ብቻ በስልክ ከምትደውል በአካል አግኝተህ የሆነ ነገር አርገህ ሳትዋሽ እውነቱን ነግረሀት ይቅርታ ብትላት ደስ ይለኛል ለምን ከዚው ውሸትን ማስመሰልን ከተለማመድከው በዃላ ከባድ ነው የሚሆነው just እንደዛ አርግ ብሮ👍
Nov 11, 2021