Hello ppl ...i know there alot of question that u have to responds here ,but may i get ur attention once... Ena getem(poem ) flge nbr malet ene tsefe menamn alkim ...ena le enat(mother )ye tesafe kal or metsaf mechel kal plz let me know ... Thanks
Nov 06, 2021ℒℴνℯ ▬ እናቴ ▬ ℒℴνℯ ቢሆንልኝማ ድካምሽን ብደክም ሸክምሽን ብሸከም ባዝልሽ በጀርባዬ ባቅፍሽ በጉያዬ ቢሆንልኝማ.......... ብሰጥሽ እድሜዬን ከኔ ላይ ቀንሼ አንቺ ጎልተሽልኝ ይዩኝ እኔ አንሼ ቢሆንልኝማ....... አንቺ እንዳረገዝሽኝ እኔም ባረገዝኩሽ በሆድ በጀርባዬ ሁለመናዬ ላይ አንቺን ባነገስኩሽ ሁሌ እንድትፈኪልኝ ደስታ እኔ በሆንኩሽ ቢሆንልኝ እማ........ እንቅፋት እንዳይኖር በተደለደልኩኝ ምቹ መንገድ ሆኜሽ ብትረማመጂኝ ህመምሽን ብወስድ ድካምሽን ብድክመው አንቺ የቻልሽውን ግን እኔ ማልችለው መስሎ የታየሽን ስቃይሽን ሁሉ እኔ ላይ ብጥይው ቢሆንልኝ እማ....... የተመኘሁትኝ አንቺነትሽን ነው እናት ያሰኘሽን ልዩ ምስጢሩን ነው ቢሆንልኝ እማ መሆን ምፈልገው አንቺኑ ብቻ ነው።
Nov 07, 2021