ሰላም ለናንተ ይሁን እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ ሰውም ሀጥያተኛ ሆነ ። እግዚአብሔርም ለነሱ ሀጥያት ሲል ሞተ። እኔ ያልገባኝ ፈጣሪ ይሞታል?
Nov 05, 2021ሰላም ለናንተ ይሁን እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ ሰውም ሀጥያተኛ ሆነ ። እግዚአብሔርም ለነሱ ሀጥያት ሲል ሞተ። እኔ ያልገባኝ ፈጣሪ ይሞታል?
Nov 05, 2021በመጀመሪያ ፈጣሪ (እግዚአብሔር) ኢ-መዋቲ (immortal) ነው። እና እንዳልከው ሰውን ከፈጠረ በኋላ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፎ ኃጥያተኛ ሆነ። ስለዚህም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ትልቅ ክፍተት ተፈጠረ። ይህ የተፈጠረው ክፍተትም ወደ በፊት መልኩ እንዲመለስ ስለሰው ልጆች ኃጥያት መስዋዕት የሚሆን ኃጥያት የሌለበት አካል ያስፈልግ ነበር (በብሉይ ኪዳን ለዚህ ሲባል ነውር አልባ እንስሳት ለመስዋእት ይቀርቡ ነበር ሆኖም ግን የሰውን ኃጥያት እስከ መጨረሻው ማስወገድ አይችሉም ነበር። [ዕብ 10:4]) ስለዚህ ከሰው ልጆች መሃል ኃጥያት አልባ የሆነ ስላልተገኘ እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ) የሰውን ልጅ ስጋ ለብሶ ወደ ምድር መጣ፣ ለሰው ልጅ ሲልም በስጋ ሞተ፣ በሞቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ ፈረሰ… ሞቶም ደግሞ አልቀረም በ3ኛው ቀን ከሞት ተነሳ። ስለዚህ ማንም በዚህ በክርስቶስ ስራ ቢያምን እና ወደ እግዚአብሔር ብቸኛ መቅረቢያ መንገዱ ኢየሱስ መሆኑን ቢቀበል የዘላለም ህይወት አለው። " ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" (የዮሐንስ ወንጌል 14:6) 🙏🙏🙏
Nov 05, 2021ፈጣሪ በባህሪዉ አይሞትም ነገር ግን የሰውን ስጋ ለብሶ ነው የመጣው የሰውን ባህሪ የራሱ አድርጓል ስለዚ በተዋሀደው ስጋ ሞቷል
Nov 05, 2021Christ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው እና የ አባቱን ፍቃድ ሊፈፅም ስለኛ ሞቷል ደግሞም የኔ ጌታ ሞቶ አልቀረም ተነስቷል 🥰😘 ወደ ጉዳይህ ስመለስ አብ እኛን ልጁን ሰውቶ ነው ያዳነን ይሄ ግን ለ አንዳንዶች ሞኝነት ነው ፍቅሩን ሊገልጥ ነው እንዲ ያረገው ዮሐንስ 3 (John) 16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ውድ anonymous 🥰
Nov 05, 2021Egziabher be sew lij amsay eghan meslo slemeta ye ghan hatiyat lemadan motual gn moto alkerem tenstual eghan be dagm msat gize new yemnenesaw esunm bsu fkad
Nov 07, 2021ፈጣሪ ሞተ ሲባል ሞተ ቀረ ማለት አይደለም። በስጋው ሞተ #በመለኮቱ ግን ህያው ነው። ለበለጠ መረጃ ሚስጢረ ስጋዌ አንብብ።
Nov 05, 2021Fitsum sew fitsum amlak silehone(hono silewerede) new berasu fekad new demo nefsun kesigaw yeleyew tenestoalim demo
Nov 05, 2021ልክ ለሰው ነፍሱ ከስጋው እንደምትለየው ነው። only difference is Christ did that separation willingly
Nov 05, 2021Mot ye sega nw nefs atmotem egziabher amlake demo be sew amsale ye sewn sega lebso weld meto teseglo be meskel lay fekrun asayto "be sega" mote! Mistere selase ena mistre segawê anbeb/temare
Nov 05, 2021Aymotm
Nov 05, 2021እግዚአብሔር አልሞተም ክርስቶስ ነው የሞተው እግዚአብሔርንና መሲሁን እየለየን እንጂ ወገን
Nov 05, 2021