ሰላም የደሴ ልጅ ነኝ በጦርነቱ ምክኒያት አሁን አዲስ ነኝ ጎደኞቼ እዛው ናቸው። ምንም የምንገናኝበት ሁኔታ የለም። ምን ላርግ በቃ በሆነው ባልሆነው ነው የማለቅሰው በጣም ከፍቶኛል በቃ ስልኬ ላይ ፎቷቸውን ካየሁማ በዙ ነገር ይመጣብኛል ምናምን ይሙቱ ይዳኑ አላውቅም ውስጤ በጣም ይረበሻል ምንም መረጋጋት አልቻልኩም አልቅሼ አልቅሼ እንኳን ሊወጣልኝ አልቻለም
Nov 04, 2021እኔም የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ እንዳንቺ እኔም አሁን አዲስ ነው ያለሁት እና እኔም ልክ እንዳንቺ ነው የሚሰማኝ ግን ምንም ማድረግ አልችልም በጣም ነው የማዝነው። በትክክል ማሰብ ሁላ አቅቶኛል ግን መቼም ቢሆን በእግዚአብሄር ተስፋ አልቆርጥም። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች! እግዚአብሔር ሀገሬን አይተዋትም! Pray for Ethiopia.
Nov 04, 2021