#የኛ አምላክ የሚታይ የሚጨበጥ የሚዳሰስ አይደለም ግን በፈጠረው ፍጥረት ባሕሪዎቹን አንፀባርቆበታል እና ይሄን ለመረዳት ደሞ አንተ ከስጋዊ መነፅር ወይም ሚዛን ወጠህ መንፈሳዊ መሆን አለብህ ቀላል ምሳሌ ላምጣል አሁን #ንፋስ ዛፉን ሲያወዛውዝ ልብስህን ሲያርገበግብ ታያለህ ገን ያን ንፋስ ባይን መመልከት ትችላለህ? አትችልም አየኽ ንፋሱን መመልከት ያልቻልከው በትንሹም ቢሆን ንፋሱ ስለ ረቀቀብህ ነው አሁን ንፋስ እንዲህ ከሆነ ያንተ ነፍስ ከነፋስ ደሞ ይረቃል ካንተ ነፍስ ደሞ መላእክት ይረቃሉ ከሁሉ ፍጥረት ደሞ ሁሉን የፈጠረው አምላክ በእጅጉ ይረቃል አየኸው አምላክ ምን ያክል ረቂቅ እንደሆነ ፍጥረት የተባለ ሁሉ አይደለም ሊመለከተው ይቅርና ብርሀኑን ሀይሉን እንኳን ተመልክቶ የሚቋቋም የለም ግን እርሱ ኃይሉ ባሕሪ በፈጠራቸው ፍጥረታት ሲያንፀባርቅ ይታያል " የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤"ሮሜ1:20-21
Nov 03, 2021