ቆይ ግን እየሱስ ዳግም ይመጣል ምትሉ ሰዎች ............. መጀመርያ ምን አስኬደው?
Nov 01, 2021(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 14) ---------- 1፤ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2፤ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ 3፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። መጀመሪያ የመጣው ስለ ሰው ልጆች ሀጢያት ራሱን መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ነበር። ለዚህም እንደ አምላክ ሳይሆን እንደ ሰው ፣ እንደ ንጉስ ሳይሆን እንደ ባሪያ ሆኖ ከሰው ተወለደ ፣ እንደ ሰው ኖረ ተገፋ ተሰቃየ ተሰቀለ ሞተ ከዛም ከሞት ተነሳ ወደ ሰማይ አረገ። አሁን ደግሞ የሚመጣው በእርሱ ያመኑትን ወደራሱ ሊወስድ ባላመኑት ላይ ደግሞ ሊፈርድ ነው። ሲመጣ ደግሞ እንደ ባሪያ ሳይሆን እንደ ንጉስ ያውም ፍጥረት ሁሉ ጌትነቱን የሚያውጅለት ሆኖ ይመጣል!!!
Nov 02, 2021