ሰላም! ታላቅ ወንድሜ ለረጅም አመታት ብቅ ጥልቅ በሚል ድብታ ተሰቃይቷል። በተለይ ኮሮና ከገባ በኋላ ከክረምት ጀምሮ ከሚወዱት ጓደኞቹ መሸሽ ፥ ከቸርች መቅረት ፥ ከዚያም ሲያልፍ እኛን ቤተሰቦቹን መዝጋት ከክፍል ወይም ሽንትቤት ሳይወጡ ለረዥም ሰዓት መቀመጥ ጀምሯል (እስካሁን ማለት ነው) ... ሶስት ሰው ብቻ በሚኖርበት ቤት አንድ ሰው እንዲህ ሲሆን ጉልህ የሆነ ተጽእኖ አለው። እኛ ቤተሰቦቹ የድብታ ህመም ሊኖርበት እንደሚችልና በባለሙያ ቢታይም ልክ እንደሌላ የጤና እክል ቀስ በቀስ ይፈታል ብለን ብናምንም ይህን ግን ወንድሜ ሊቀበለው አልቻለም። አሁን እርሱ ያለበት ሁኔታ ከስነልቦናዊ ነገር ጋር ንክኪ እንዳለው አያምንም። ይልቁንስ የማመናፈስ አዝማሚያ አለው። ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄድ ብንወተውትም "ተውኝ!"፤ "አልሄድም ብያለሁ አልሄድም" ከሚል ቁጣ የቀላቀለ መልስ ውጭ ምንም አናገኝም። ታዲያ ወንድሜ፥ ይህ ችግር ሊኖርበት እንደሚችል አውቆ እርዳታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ እንዲሆን ምን እናድርግ?
Nov 01, 2021ante wendmehn lemekreb mokr yerasehin ye ken wlo bemawrat esu ye esun huneta endiyawerah lemaberetatat mokr egziabher yrdachu
Nov 02, 2021