#relationships ሰላም✋ ፍቅረኛ ነበረችኝ። ከኔ በፊት ፍቅረኛ ነበራት። ጥሏት ሄደ በርካታ ጊዜያት መርሳት ሳችል ቀርታ ተጎዳች። በመሀል ከ እኔ ጋር ግንኙነት ጀመርን። ወደ 5ወር ከኔ ጋር ጥሩ የፍቅር ጊዜያት ካሳለፍን በኋላ ድንገት ስሜቴ ጥሩ አደለም ከምትጎዳ እንለያይ አለችኝ። እኔም ለሁለታችን ስለሚጠቅመን መለያየትን መረጥኩ። ነገር ግን ከተለያየን ጀምሮ ሳላስባት ውዬ አድሬ አላቅም፤ ባሰብኳት ቁጥር መጠቀሚያ እና ሀዘኗን ማስረሻ አድርጋኝ እንደሄደች ስለማስብ በየቀኑ እናደዳለሁ ነገሮችን መርሳት አልቻልኩም እንዴት መርሳት እችላለሁ???
Oct 29, 2021እንደዛ ማሰብ የለብኽም። ልጅቷ የምታፈቅረውን ሰውም ብታጣም አንተ እሷ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ጥሩ ስብዕና ስላለኽ ልታፈቅርኽ ሞክራ ነበር። ሆኖም ግን ከአቅሟ በላይ በመሆኑ ብቻ ልትጎዳኽ ስላልፈለገች ያን እንድትወስን ሆናለች መረዳት ይኖርብካል።አንተም ወንድሜ #ህመም ቢኖረውም ለአንድ ሰው ህመም ማስረሻ መድኃኒት እንደመሆን የሚያስደስት ነገር አለመኖሩን መረዳትና አሜን ብሎ ተቀብሎ ማለፉን መልመድ ይኖርብኻል።ይኽ ማለት ግን ህመምኽን ለመርሳት ሌላን ሰው መጠቀሚያ ማድረግ ይኖርብካል በቀጣይ ማለት አይደለም። ለራስኽ ግዜ ስጥ ስራኽ ወይ ትምህርትህ ላይ አተኩር ። ይስተካከላል። እሷን ለመርሳት ማድረግ ያለብኽ ነገር ቢኖር አንተ እንዳሸነፍክ ማመን ነው።
Oct 29, 2021