ሰላም ወንድም እና እህቶቼ የሰንበት ተማሪ ነኝ እና ዲያቆን እና ካህናት ልዩነቱ ምንድነው እና ለመሆን ምን ያስፈልጋቸዋል? የምታውቁ ብታስደረዱኝ
Oct 27, 20211)ዲያቆን የመጀመሪያው የክህነት ትንሿ ሥልጣን ናት። ካህንነት ደግሞ ከዲቁና ከፍ ያለ ሥልጣን ነው። 2) ዲያቆናት መንበሩን መንካት አይችሉም። ካህናት ግን ይችላሉ። 3) መፍታት ማሰር የተሰጠው ለካህናት ነው ለዲያቆናት ግን አይደለም። 4) ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን መፈተት ወይም መንካት የሚችሉት ካህናት ብቻ ናቸው ዲያቆናት ግን አይደሉም። 5) ካህናት ዝቅ ብለው ዲያቆናት የሚያደርጉትን ሁሉንም ስራ መስራት ይችላሉ። ዲያቆናት ግን ከፍ ብለው ካህናት የሚያደርጉትን ነገር በሙሉ ሊያደርጉ አይችሉም። እያለ በርካታ ልዩነቶች በውስጣቸው አለ ይህ ከብዙ በጥቂቱ ነው ወንድሜ🙏
Oct 29, 2021