እኔነት ጊዜ እንደጉም በናኝ እኔ የህይወት መናኝ የህይወቴ ጎዳና ዙሪያገባው መንገድ መሀሉ ጠፍቶብኝ ከጥግ የምንገዳገድ ከነብሴ አዝመራ ጥላቻን ስለቅም "ቀርቶ የማይጎዳ፤መጥቶ የማይጠቅም" ከሚል ቅፅል ስሜ በፍፁም አልርቅም.. እኔ... የትውልድ ተገፊ የሀዘን ርጋፊ ማንነቴ ዝቃጭ ለሰው-ነት ማልታጭ አይዘንብ አያባራ፤ ኑሮዬ ደመና ያለ ብርሀን ምትኖር ነብሴ በገመና የመወደድ ስሜት ጠብታ ማይደርሰኝ እርባና ቢስነት አንጀቴን ሚያርሰኝ እያለው ማልታይ ፤ ሳልታይ ምጠላ ልቤም የከሸፈ ፤ ላዬም በድን ገላ መርገምት ነው እኔነት የጠለሸ እምነት ጎዶሎ ማንነት ጎብኚ እንዳልተጠጋው የረገፈ መስህብ ውስጤ የፈራረሰ እውቀቴም የነሲብ ናፋቂ ማጣቴን መረሳቴን ያመንኩ በ"አስታዋሽ አጥ ገዳም" ያለእድሜዬ የመነንኩ እኔ ... እኔ የአረም ብቃይ ዘመኔም የስቃይ የራሴ አለም ታካች፤የምኞቴ መካች የሰው ኑሮ አዳማቂ፥የበይ ተመልካች👐 That's how deep i feel about my self👈 can any one relate?
Oct 27, 2021ግጥሙ እንደ ግጥም አሪፍ ነው።ግን እራስህን/ሽን በዚ ግጥም ውስጥ አትመልከት/ቺ፤ከጨለማ ጀርባም የብርሃን ተስፋ እንዳለ አይገልፅም።
Oct 28, 2021