ያገሬ ሰዎች.....ጥያቄ ነበረኝ የግቢ ተማሪ ነበርኩ ግድ ማቋረጥ ነበረብኝና አቋረጥኩ ከዛ ኮሌጅ ከአዲስ ጀመርኩ አሁንም ግን የግድ የማቋርጥበት ምክኒያት ተፈጠረ እና ላቆመው ነው(በገንዘብ እጥረት ምክኒያት) እንዲ እያልኩ 3 አመት ባክኖብኛል እና ትምህርት ለኔ አልተፈጠረም ብዬ ልተወው እና ፊቴን ወደ ስራ ላዙር ወይስ በድጋሚ ወደ ግቢ ተመልሼ ልቀጥል በያመቱ ፍሬሽ መሆንም ከበደኝ ግሬዴ ደግሞ አሪፍ ነው ጎበዝ ከሚባሉት ነኝ በገንዘብም የግድ እራሴን መደገፍ አለብኝ 1 መንገድ ላይ መመላለስ ነው የሆነብኝ ደክሞኛል በጣም ግራ ገብቶኛል ሞራሌም ሞቷል ምን ትመክሩኛላችሁ እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላቹ?
Oct 25, 2021ምትሰሪው ስራ ፋታ ሚሰጥሽ ከሆነ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ብታስኬጂው ጥሩ ነው።ካልሆነ ግን በቃ ስራውን ስሪ፤ምክንያቱም አሁንም የገንዘቡ ችግር ካልተፈታ ትምህርቱን ብትቀጥይ እንኳን ድጋሚ አለማቋረጥሽን ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ? ደሞ እዚህ ሀገር ተመርቀሽ እራሱ ስራ ማግኘቱ ሌላ ጥያቄ ነው።ስራውን እየሰራሽ ገንዘብ ስታገኚ የርቀት መማር ትችያለሽ።
Oct 26, 2021