selam orthodox tewahdo yehonachiw kalachiw eski ye erasachiw yemtwodutn mezmur lakulgn
Oct 25, 2021✞ከሊባኖስ✞ ሐና እና ኢያቄም ወለዱ ሰማይ አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደኛ(፪) ተጨነቀ አዳም በመከራ በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ የፍጥረቱ ዕንባ በመስቀል ታበሰ(፪) አዝ= = = = = የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ ለቀደመች ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም(፪) አዝ= = = = = ጽኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ በሐና ልጅ በኢያቄም ፍሬ ደስታ ሆነ ቅኔ እና ዝማሬ(፪) አዝ= = = = = በወለዱሽ በሐና በኢያቄም ተማጽነናል ድንግል ማርያም ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት ልጆችሽን ጠብቂን ከጥፋት ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት ኢትዮጵያን ጠብቂያት ከጥፋት መዝሙር ዲያቆን አቤል መክብብ "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤" መዝ፹፮፥፩ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯