የህይወት ግብ ምንድነው ህይወት ትርጉም የለሽ ሆናብኛለች እራስየማጥፋት ሀሳብ ብቻ ነው ያለኝ እየኖረ ያለ ሰው አለ ለመኖር ከመፍጨርጨር ውጪ
Oct 24, 2021እኔ በምን እንደምጽናና ታውቃለኽ ወንድሜ። ሀዘን እንደሚያልፈው ደስታም እንደሚያልፍ ሳስብ ለቅሶ እንደሚያልፈው ሳቅም እንደሚያልፍ ሳስብ በሚያልፍ ቀን ውስጥ የማያልፈውን እግዚአብሔርን ሳስብ በዚኽ እጽናናለው። ከዚኽ ደሞ ካለፈ ሀዘኔ እንደሚያልፍ አስቤ ሀዘኔ ባያልፍ እንኳን እኔ እንደማልፍ አስባለው እናማ በሚያልፍ ሀዘን አልያም በማለፍ እኔ መካከል ያለውን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው። ራሴን ማጥፋት ግን አይታሰበኝም በዋጋ የተገዛው የክርስቶስ ልጅ ነኝና እኔ በኔ ላይ ስልጣን የለኝም።ፈጥሮ የላከኝ አምላክ እስኪወስደኝ ድረስ ሙሉ መብቱ የፈጣሪ ነው። # ሕይወትን ጣፋጭ የሚያደርገው በራሱ ትግል ነው። አይዞን
Oct 24, 2021