ሰላም ኦርቶዶክስ እህትና ወንድሞቼ ፤ የ 22 ዓመት ሴት ወጣት ነኝ። ሁሌም ድብርት ፣ ሰውኛ ያልሆኑ ክፉ ሀሳቦች እና ህይወቴን መጥላት ሲፈታተኑኝ ኖረዋል ፤ እና ፀበል ብዙ ጊዜ ባልሄድም ስሄድ ቀለል ይለኝ ነበር። አሁን ግን መሄድ ራሱ አልቻልኩም ፤ ጭንቅላቴ በጭንቀት ሊፈነዳ ነው። ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል ፤ አለመኖር ብቻ ነው የምፈልገው። ቤተሰቦቼ አይገባቸውም አብራርቼ ላስረዳቸውም አልችልም፤ አዕምሮዬን አውርቼ ማረጋጋው ጓደኛም እንኳን የለኝም ፤ በዚያ ላይ ሆዴን በጣም እያመመኝ ተቸገርኩ። በአንዱ ስለው በአንዱ ፤ ሁሉ ነገሬ ተያዘብኝ። እባካችሁን ምን እየሆንኩ ነው ? የሆነ መውጫ መንገድ ጠቁሙኝ ቢያንስ አዕምሮዬ ተረጋግቶ ፀሎት እና ፀበል እንኳን እንድጀምር ምን መፍትሔ አለው?
Oct 23, 2021እህቴ የመምህር ተስፋዬ አበራ ገጠመኝ የሚለውን ትምህርት YouTube ላይ ካዳመጥሽ በሗላ ውስጥሽ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ጀረጃ ትረጃለሽ። ስለእውነት ነው የምልሽ ይህን ትምህርት አዳምጪው ይጠቅምሻል ስለህይወት ያለሽ አመለካከት ይቀየራል። እውነት ከምር ነው የምልሽ ይህን ያህል ስለራስሽ የምትጨነቂ ከሆነ ትምህርቱን አዳምጪው። የምትፈልጊ ከሆነ ልልክልሽ እችላለሁ ።
Oct 23, 2021