አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአዲስ አበባ በሚገኙ 55 ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ እየተተገበረ ነው። የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በከተማዋ በሚገኙ 11 የሁለተኛ ደረጃ እና 44 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላት ገልጸዋል። በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ስርዓተ ትምህርቱን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል። የትምህርት ጥራትን ማምጣት ትኩረት ያደረገው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ አገር በቀል እውቀት፣ ግብረ ገብ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የመንገድ ደህንነትና ሌሎች ትምህርቶችን ያካተተ ነው። የሙከራ ትግበራው የትምህርት ተደራሽነት፣ የተገኙ ለውጦች እና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮችን ለመለየት ያስችላል ተብሏል።
Oct 19, 2021