እስኪ ፂሆን ማለት በእውነት ድንግል ማርያም ነች ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን እባካቹን አስረዱኝ?? ወንድማቹንም ከውዥንብር አላቅቁኝ!?
Oct 17, 2021በ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከ 150 ጊዜ በላይ ጽዮን የሚል ቃል አለ። ግን ይህ ሁሉ ጽዮን የሚል ቃል እመቤታችን ድንግል ማርያምን አይወክልም። ግን አራት ነገሮችን ይወክላል። 1, ከ 76 ጊዜ በላይ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ጽዮን ተብላ የተጠራችው የ ዳዊት ከተማ ናት። 2ኛ ሳሙ 5፥6 ሚኪያስ 3፥12 ኢሳ 64፥10 2, ጽዮን እየተባለች በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከ 4 ጊዜ በላይ የተጠራችው የ ጌታ ዙፋን የተዘረጋባት ሰባተኛዪቱ ሰማይ ጽረ አርያም ናት። መዝ. 49፥2 ራዕይ 14፥1 3, ጽዮን እየተባሉ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከ 25 ጊዜ በላይ የተጠሩት ቤተ እስራኤል, ቤተ አይሁድ በ ጽዮን ከተማ የሚኖሩ ህዝቦች ናችው። መዝ. 147፥1 መዝ. 111፥13 ኢሳ 3፥ 16 4, በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ 4ኛዋ ጽዮን ተብላ የተጠራችው ምስጋናዋ ከምስጋና በላይ የሆነው የ አምላካችን እግዚአብሄር እናት ድንግል ማርያም ናት። ኢሳ 59፥ 20 ሮሜ11፥26 መዝ. 86፥5 👆ግልጽ ነው ብዬ እስባለሁ 😊
Oct 18, 2021