Eski sewoch mtawku kalachu tarik 1,Tewodross || snt battle lay tesatfal ena battlum keman kaman ga new 2, yohaniss |v snt battle tewagtal ena keman kemanga new 3,Menllike || Snt battle tewagtal keman kemanga please mtawku kalachu nigerugn please
Oct 17, 2021እሺ የማቀውን ልንገርህ ከተማርኩት የ 11ኛ ክፍል social ተማሪ ነኝ!! አፄ ቴውድሮስ || (1855-1868) ትክክለኛ ስሙ ካሳ ሀይሉ በመጀመሪያ ሁሉም መሪዎች በሀገር ውስጥ ስልጣን ለመያዝ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ ሰዎች ጋር ተዋግተዋል። በ1848 ቴውድሮስ ደባርቅ ላይ በግብፅ ተሸንፏል።የተሸነፈው በዘመናዊ ጦር መሳሪያ ተበልጦ ስለሆነ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ሀገር ውስጥ ለማምረት ፍላጎት አሳየ ...... በሚያዚያ 10, 1868 ከእንግሊዝ ጦር ጋር በመቅደላ (ኤርጎሄ) የተዋጋ ሲሆን በጦርነቱም ተሸንፏል። አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1868-1871) ትክክለኛ ስሙ ዋግሹም ጎበዜ እኚህ አፄ ከውጭ ጠላት ጋር አልተዋጉም አፄ ዮሀንስ IV(1871-1889) ትክክለኛ ስሙ ካሳ መርቻ ህዳር16 , 1875 ኢትዮጲያ ከግብፅ ተዋግተዋል ጦርነቱንም ኢትዮጲያ ናት ያሸነፈችው።ጦርነቱም የ ጉንደት ጦርነት(the battle of gundet) ይባላል። መጋቢት 7-9 ,1876 ኢትዮጲያ ከግብፅ ተዋግተዋል ጦርነቱንም ኢትዮጲያ ናት ያሸነፈችው።ጦርነቱም የጉራ ጦርነት (the battle of gura)ይባላል። ከሱዳኖች ጋር ደግሞ ከ 1885-1889 ድረስ አራት ጦርነቶች ተካሂደዋል። መጀመሪያ የተካሄደበት ቦታ ኩፊት ሁለተኛ የተካሄደበት ቦታ ጉቲ ዲል ሶስተኛው የተካሄደበት ሳርውሀ አራተኛው የተካሄደው መተማ ነው። አፄ ዮሀንስም የተገደለው በመተማው ጦርነት ላይ ነበር። አፄ ሚኒሊክ (1889-1913) አፄ ሚኒሊክ የተበታተነቸዋን ማለትም አንድ ወጥ ገዢ ኢትዮጲያ ስላልነበራት ሁሉንም በአንድነት ለማምጣት ሀገር ውስጥ ካሉት ገዢዎች ጋር ጦርነት አካሄዷል። ምንም እንኳን ስልጣን የያዘው በ 1889 ይሁን እንጂ ውስጥ ውስጡን ከ ዮሀንስ ስር ሆኖ ከሸዋ ተነስቶ ወደሌሎች ቦታዎች ግዛቱን እያስፋፋ ነበር ለምሳሌ ከ 1875-1889 ድረስ ሀረር፣አርሲ ፣ወለጋ፣ኢሉባቡር...ወዘተ.. ተቆጣጥሮ ነበር በአጠቃላይ ከ 1875 -1900 ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ ኢትዮጲያን በራሱ ስር ለማድረግ ተንቀሳቅሷል በመጨረሻም በ1900 አጠናቋል። ታህሳስ 7,1895 ከ ጣሊያን ጋር ተዋግቷል ።አሸናፊዋም ኢትዮጲያ ነበረች። ጦርነቱም የ አምባላጌ ጦርነት(the battle of ambalage ) ይባላል። መጋቢት 1,1896 ከጣሊያን ጋር በድጋሚ ተዋግታለች ።አሸናፊዋም ኢትዮጲያ ነበረች ።የጦርነቱ ስምም የአድዋ ጦርነት(the battle of adwa) ይባላል። Note ፦ ሁሉም አመተ ምህረት በውጮች አቆጣጠር ነው ።
Oct 17, 2021