ሪዎናልዶ ዳቪንቺ የሳለው ከሐዋርያቱ ጋር የክርስቶስ የመጨረሻ እራት የሚለው ስእሉ ላይ ከክርስቶስ ጎን የተቀመጠችውን ትኩር ብላችሁ ካያችኋት የሴት ገፅታ እና አቋም ነው ያላት...ጥርጣሬን የሚያረጋግጡ ፅሁፎችንም በኢንተርኔት በብዛት አግኝቻለው እንዲሁም ሴቷ ማርያም መግደላዊት እንደሆነች...ጥያቄዬ በብዛት በየቤታችን የሚገኘው ይሄ ምስል በቤተ-ክርስቲያን ይታወቃል/ጥቅም ላይ ይውላል ወይ? ከዋለስ በአስተምህሮቱ የምናውቀው ክርስቶስ ከሐዋርያቱ ጋር ብቻ የመጨረሻውን እራት እንደፈፀመ ነው.. በአጠቃላይ እስኪ ምን ታስባላችሁ ምስሉን ተመልከቱና?
Oct 15, 2021ይሄንን መሰል በክፍላሀተ ሀገራት የሚገኙ አጥቢያዎች እንደሚጠቀሙ አይቻለሁ የዳቬንቺን የሚጠቀሙት ገንዘብ በቅናሽ የሚሰሩላቸውን የኦርቶዶክስ የአሳሳል ዘይቤን ጠንቅቀው ያልተማሩ ድኩማን ያዩትን የሚገለብጡት ናቸው ኢቭን በዳቬንቺ ንድፍ የተሰሩ አለም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አሉ ግን አንተ ያነሳኸውን እና ሌሎች ኮንትሮቨርሻል ጉዳዮችን አስወግደው ነው የሚስሉት እና የማቀርፁት እስፔሻሊ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያናት
Oct 16, 2021