Selam sewech mirt yetebale night club ngerugn leketemaw fresh negn 🙄🙄🙄
Oct 15, 2021የከንቲባው ልጅ "ወይ አዲስ አበባ" እያለች ትገረማለች ። ከዛን ወደኔ ዙራ "ስማኝማ ፡ ፈታ ልንል ነው አይደል ይሄን ሁሉ ርቀት አቋርጠን የመጣነው ...?" አለችኝ ። አዎ ስላት "እንደዛ ከሆነ ፡ በናትህ ፡ ስወድህ ፡ night club ውሰደኝ" አለችኝ ። "ጀማሪ እረኛ ፡ ከብት አያስተኛ" ይለዋል የሀገሬ ሰው ። ልጅቷ እቤት ሆና በፊልም ያየችውን ነገር ባካል ማየትና ማድረግ ትፈልጋለች ። ደግነቱ ከያዝነው ሆቴል አጠገብ club ይታየኛል ። እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደዛው አመራን ። entrance / መግቢያ ከፍለን ፡ ተፈትሸን ገባን ። ጎበዝ ፡ ወጣቱ እዚህ አ እንዴ ያለው ። ለካ ኢትዮጵያ ወደ ዋላ የቀረችው ወዳ አይደለም ። መደማመጥ የለም ፡ ጭፈራ ብቻ ነው ። የእስፒከሩ ጩኸት ፣ የሰው ጫጫታና ዳንስ ቦታውን ሶሪያ አስመስሎታል ። "እንቅስቃሴዎች ሁሉ dance ናቸው" የሚለውን ዘፈን teddy yo እዚህ ቤት ቁጭ ብሎ የፃፈ ይመስላል ። እኔ እንኳን club ስገባ የመጀመሪያዬ ስለሆነ ስራቴን ይዤ ቁጭ ብያለሁ ። ባይሆን መጠጧን አንድ ሁለት እያልኩኝ ፡ ትርዒቱን እያየሁ ልምድ እየቀሰምኩ ነው ። ልጅት ደግሞ በስሜት አሸሸ ገዳሜውን ለመቀላቀል #1mm ነው የቀራት ። "ሂድልኝ ሀዘን ጭንቀቴ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ ፣ ጥፋልኝ ሀዘን ህመሜ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ" ። ብቻችሁን መምጣት ክልክል ነው የተባለ ይመስል ፡ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የመጡት (ልክ እንደኛው ...🙈) ። የፈራሁት አልቀረም ፡ የከንቲባው ልጅ እጄን ይዛ አስነስታኝ ትርዒቱ መሃል ቁጭ (ይቅርታ ቁም ለማለት ነው ...🙆) ። እንቅስቃሴ ጀምረናል ፡ ለነገሩ dance ላይ ብዙም የስራ ልምድ ስለሌለኝ እየጨፈርኩ ሳይሆን እየተወላገድኩ ነው ብል ይቀለኛል ። በመሀል በመሀል አንድ ሁለቱን ፡ ሶስት አራት እያልነው ነው ። ፊልም ላይ አረቄ /Jin ባንድ ትንፋሽ እንደዛ ሲጨልጡት በውሃ የሚያታልሉን ይመስለኝ ነበር ። ዛሬ ግን በአይኔ በብረቱ አይቼ አምኛለሁ (አይን ብረት ነው እንዴ ...🙄) ። ኧረ ሴቶቻችን ተበላሽተዋል ጎበዝ ። ከወንዶቹ ይልቅ እነሱ ባሱኮ ። የሌሎቹ ሲገርመኝ የኔዋ ጉድ ብሳ ተገኘች ። እየጠጣን ፣ እየጨፈርን ፣ እያረፍን ፣ በድጋሚ የአሁኑን step እየደገምን በስተመጨረሻ ልጅቷ ውሃ ሆና እላዬ ላይ ተዘረገፈች ። እንዴት ተሸክሜያት ከክለቡ እስከ ያዝንበት ሆቴል እንዳደረስኳት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው (እኔም ግን አውቃለሁ ...😜) ። በስንት ድካም የያዝነው ክፍል ደረስንና አልጋው ላይ ዘረገፍኳት ። ንሰሐ ገብቼ ሀጥያቴን የተናዘዝኩ ያክል ነው ቅልል ያለኝ ። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ገላዋን ሙሉ በሙሉ የመሸፈን አቅም አልነበረውም ። በቀላል maths ከወገብ በታች አካሏ #80% ይታያል ። አልተን ገዳገድኩም እንጂ መጠጡ አናቴ ላይ ወጥቷል...✌️
Oct 16, 2021