Sewoch✋ Semonun mnm tru eyetesemang aydelem yekoye bedel eyabseleselku yemeshenef smet yisemangal erasen le bekel betam eyegefafahut new mkr yemiyagzeng kehone yehone neger belung please💔😔
Oct 12, 2021ደካሞች_ይቅርታን_አያውቋትም ➦ ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። ➦ አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ➦ እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ➦ ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል። ➦ አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ➦ ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና- ሰላም ህልውናችን ነው ! #ይቅርታ ብለክ ተወው እርሳው
Oct 13, 2021