Sele kokeb mn yahlachu tawkalachu be kokeb yemiyamn esti liyamn yechalebetn mknyat yasredagn sele melkam melsachu tnx
Oct 12, 2021አንድ ነገር ልንገርሽ። 12ቱም አውድ-ወርኅ ውስጥ universal የሆኑ ባሕርያት ስላሉን አንዱ የmind game አካል ነው። አሁን የ12ቱንም zodiac ብናነብ ከያንዳንዱ የራሳችንን ባሕርይ እናገኝበታለን። አንዱ ኮከብ ተናዳጅ ነው ይላል- አዎ ባንዳንድ ነገሮች ቶሎ እናደዳለው፥ ሌላኛው ኮከብ ደሞ ተጫዋች ነው ይላል- አዎ ተጫዋች ከመሆነ የተነሳ የግል መጠርያ አለኝ፥ ሌለኛው ኮከብ ደሞ ዝምተኛ ነው ይላል- አዎ በጣም በሚለይ መልኩ ከሰው ጥያቄን የማላስተናግድበት ዝምታም አለኝ፥ በሌላኛው ደሞ የሚፈራ ነው ይላል- አዎ ታላላቄ ሆነው ሳሉ በጣም የሚፈሩኝ ብዙ ሰዎች አሉ፥ በተቃራኒው አንዱ ኮከብ ሁሉም ይዳፈረዋል ሲል አውነቱን ነው- ይኸው አናቴ ላይ ፊጥ ያሉ ስንት መዓት ሰዎች አሉ፥ ወሸት ይጠላል ይላል- በተለይ ማስመሰል እና ግልጽ ውሸት በጣም ምርር ያደርገኛል፥ አንዱ ላይ ደሞ ውሸታም አለኝ- እውነት ነው፤ ሳልተኛ ተኝቻለው የምለው ራሱ አራሱን የቻል ውሸት😢። አሁን እንግዲ የኢትዮጵያውያኑም ሆነ የግሪኩን (ታዋቂው zodiac) ሁለቱንም አይቻለው። ግን ሁለቱም ስለኛ ህይወት ይወስናሉ የሚለውን በጭራሽ አልቀበለም። We are how our societies and environment brought us up!
Oct 12, 2021