እኔ እምለው አንደ ፕሮቴስታንት ሀይማኖት አበባል ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ እንጂ በህግ በመፈፀም በበጎ ምግባር በትሩፋት በምስጢራትን ቀመፈፀም በፆም በፀሎት አይደለም ከተባለ .... ጌታችን የሰውን ልጅ ሥጋና ደም ካልበላችሁ የዘላለም ሕይወት የላችሁም ፤ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ፤ ንስሐ ባትገቡ ትጠፋላችሁ እያለ ያስተማረን ትምህርቶች ዋጋ የላቸውም ማለት ነው? ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ትእዛዛትን ጠብቅ (ማቴ 19፥17) እንዲሁም ትእዛዜን ጠብቁ ነው ያለው ። ዮሐ 14፥15 ሌላው ፅድቅ በእምነት ብቻ ለምትሉ ወገኖች" እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱ እንደሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ" ራእ 22፥12 ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም "እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ አንደሆነ እንዲሁ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው" 2፥14-26 በማለት ነው የሚነግረን ሌላም ስለእምነት እና ስራ ማየት ከፈለጋችሁ ማቴ 16፥27 , 2ቆሮ 5፥10 , ሮሜ2፥5 , ኤፌ 6፥8 , ኤር 1710 ,ራእ 2፥24 , ዮሐ 5፥29 , 1ኛ ጴጥ 4፥18 እነዚህን ማየት ይቻላላል እስኪ ንገሩኝ ሌላ ሳትዘባርቁ መጀመርያ ይህን አስረዱኝ እና ጥያቄ ካለ ጠይቁኝ ዝምብላችሁ እዛች የሸመደዳችኋት ጥቅስ ላይ አትሩጡ
Oct 12, 2021ከላይ በደንብ አስረድተዋል ግን ይሄን ልንገርህ፡ ህግ ፅድቅን ሊሰጠን ይችላል? ፅድቅ ማለት justified mehone ማለትም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ማግኘት ማለት ነው። ታዲያ ህግ ፅድቅ ሊሰጠን ይችላል? ማይሰጠን ከሆነስ ለምን ህግ ተሰጠን ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል ,,,,,,, ህግ ለህይወት እንዲሆን ታስቦ ተሰጠን፤ ህግ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ጥላውን ነገረኝ። ግን ህግ ለህይወት ታስቦ የተሰጠን ቢሆንም ግን እኛ ላይ ሞትን አመጣብን ምክንያቱም ከህጉ አንዱን ብትተላለፍ ሁሉን እንደተላለፍክ ተደርጎ ይቆጠራል። ማንም በህግ ሊፀድቅ አልቻለም ቢፀድቅ ኑሮማ ክርስቶስ መምጣት ባላስፈለገው ነበር። ግን ህግ በእኛ ውስጥ ሊፈፅም ያልቻለውን ነገር በክርስቶስ ተፈፀመ፤ ይሄም ፅድቃችን ነው። ,,,,,,, ይሄ እንደ ሰው ሲታይ ሞኝነት ይመስላል ግን የእግዚአብሔር ጥበብ በዚ ተገልጦዋል። የእግዚአብሔር ጥበብም ኃይልም ክርስቶስ ነው ለዛ ነው፤ በርሱ በኩል የመዳኛ መንገዳችን ተሰራልን። ይህም ዮሐ 3፥16 ነው። ወንድሜ እኔ ልንገርህ እኛ በእምነት ፀድቀናል ብለን ስጋውና ደሙን አልተውንም ወይም ትዕዛዙንም አልጣስንም። እነዚህ ነገሮችን ምንፈፅመው ህግ ሆነውብን ግዴታ ስለሆኑ አይደለም ግን በውስጣችን ያለው መንፈስ እንኩዋ እነዚህን ነገሮች እንድናረግ ያስገድደናል። እናንተ ከምትሉዋቸው መልካም ስራዎች ሁሉ ምንም አናጎድልም ግን ምንሰራው ሁሉ ስለዳንን ነው። የነገርኩህ ሁሉ ሮሜ ላይ ቆሮ ላይ ኤፌሶን ላይ አለ። የምር እንድትረዳኝ ሃሳቤን በጣም እፈልጋለሁ ጌታ ይርዳህ
Oct 12, 2021