Is there an orthodox here who can tell me why we have to repent to nitsha abtoch and why not repent to god?
Oct 11, 2021ለምንፈጽመው በደል ማስተስረያ እንዲሆነን ለሐዋርያትና እነሱን ለሚከተሉት ካህናት ሥልጣንን በመስጠት ምሥጢረ ንስሐን መሥርቶልናል። ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን የእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ለእኛ ጥቅምና ደህንነት ሲል ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለጴጥሮስና ለሐዋርያት ተከታዮች ሰጥቷል። ቅዱስ ጴጥሮስ ስለእውነተኛ እምነቱ ከመሰከረ በኋላ ሥልጣነ ክህነትን ማለትም የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ክርስቶስ ሰጥቶታል። እንዲህም ብሎታል «የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል» /ማቴ. ፲፮፥፲፱/። እንደዚሁም ይህን ሥልጣን ለሌሎች ሐዋርያትም ሰጥቷቸዋል። /ማቴ ፲፰፥፲፰/። ከትንሣኤው በኋላም ለሦስተኛ ጊዜ ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል። «አብ እኔን እንደላከኝ እኔም ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ይህንንም ብሎ እፍ አለባቸውና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።» /ዮሐ. ፳፥፳፩-፳፫/። ስለዚህ ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን ለነሱ የተሰጠ ስለሆነ በሐዋርያት እግር ለተተኩ ለቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናት ኃጢአትን መናዘዝ ይገባል።
Oct 12, 2021