Selam endet nachehu... wedetyake segeba ye amargna fidelat lay double yehonu fideloch ሀሐ ሠሰ አዐ ጸፀ... kenezih west lemsale ሐ፣ሠ፣ዐ aletekmachewem ena meche ena mn aynet Kal lay nw migebut?kg gbi mnamn tlu yehonal eko😁
Oct 10, 2021አማርኛ ከግዕዝ ቋንቋ ጋር በአመዛኙ በጣም የቀረበ ቁርኝት አለው። ይኸውም ቃላትን በመዋስ፤ የእርባታ መንገዶችን በመዋስ ይገለፃል። ቃላትን በሚዋስበት ጊዜ የሚፃፉበትንም ፊደላት አንድ በአንድ መውሰዱ አይቀርም ይህ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከላይ የጠቀስሻቸውን ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸውን ጥንድ ፊደላት የሚጠቀሙ ቃላት ሲኖሩ በአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም ላይ ግድ የለሽነት ይስተዋላል ይኸውም አንዱን በአንዱ መለወጥ ነው። ለምሳሌ፥ አመት እና ዓመት፣ በአል እና በዓል ወዘተረፈ ይህ አይነቱ ድርጊት ብዙ ጊዜ የትርጉም ለውጥ ላያመጣ ይችላል ነገር ግን ከላይ በሰጠሁት ምሳሌ ላይ ትልቅ የትርጉም ለውጥ ሲያመጣ እና ተናጋሪው ከመሰረተው ዓውድ ጋር ሲቃረን ይስተዋላል። ምሳሌ፥ መልካም በአል፤ መልካም አዲስ አመት ወዘተረፈ እነዚህ ሁለቱም ምስረታዎች የተሳሳተ የፊደል አጠቃቀም ይታይባቸዋል።
Oct 11, 2021