Selam sewoch የስላሴ አንድነት ሶስትነት በምሳሌ የሚያስረዳኝ amsgnalew 😊 Dmo mnm ngr disproof lmarg adlm
Oct 09, 2021የሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት 🍀አንድነት: በመለኮት በባህሪ በህልውና በፈቃድ በእዘዝ በአገዛዝ ይህን ዓለም በመፍጠር ፈጥሮም በማሳለፍ በመሳሰሉት አንድ ነው። 🍀ሶስትነት: በስም በአካል በግብር እና በኩነት ሶስት ናቸው። ምሳሌ: ፀሀይን ውሰጂያት ክበብ አላት ብርሀን ትሰጣለች ሙቀት ታመነጫለች👉ክበቡ በአብ ይመሰላል ብርሃኑ በወልድ(አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም ብሏልና) ይመሰላል ሙቀቱ ደሞ ሕይወት በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል 👉ስለዚህ ፀሀይ እንደእነዚ ሶስት ነገሮች ኑሮአት ሶስት ፀሀይ አትባልም አንድ ነው እንጂ ስለዚህም አብ ፀሀይ ነው ወልድ ፀሀይ ነው መንፈስ ቅዱስ ፀሀይ ነው እና እግዚአብሔር በስም በአካል በግብር በኩነት ሶስት ብንልም ሶስት እግዚአብሔር አንልም አንድ እግዚአብሔር እንላለን። በመፅሐፍ በጣም ብዙ ቦታዎች ተገልጧል የሥላሴ ሚስጥር ዘፍ1:26,ዘፍ3:22, ዘፍ18 ብታነቢው, ማቴ.3(መጨረሻ አካባቢ),2ኛ ቆሮንቶስ13:14....የመሳሰሉትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል እሕቴ ፈጣሪ ያክብርልኝ🙏
Oct 10, 2021