Hi everyone አንድ ሰው በ ህልመ ለሊት ከወደቀ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ መግባት መስቀል መሳለም ይቻላል ወይ ?? Please melisulign🙏🙏
Oct 09, 2021★ "ዝንየትና" መንፈሳዊ ሥርየቱ በየትኛውም ሁኔታ ዝንየት ያገኘው ሰው በዚያው እለት ሥጋ ወደሙ በቀበል (መቁረብ) አይችልም፡፡ አንድ ሰው ሌሎች ለቁርባን የሚደረጉ ዝግጅቶችን ያሟላ ቢሆንም ሕልመ ሌሊትን በማየቱ ብቻ ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ብቁ አይሆንም፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ የሚከለከለው ከቅዱስ ቁርባን ብቻ አይደለም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመግባትም ይከለከላል፡፡ ለመግባትም የሚፈቀድለት ልብሱን ካጠበ ወይም ከቀየረና ገላውን ከታጠበ በኃላ በማግስቱ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ገጽ ፳፬) ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይቻልም ማለት ስለ ወር አበባ በሚያትተው አንቀጽ እንደተገለጸው ወደ ቤተ መቅደስ አይግባ እንጂ የመጀመሪያውን ቅጽረ ቤተክርስቲያን ዘልቆ በመግባት ጸሎት፣ ትምህርትና የመሳሰሉትን መንፈሳዊ ተግባራት፣#መስቀል መሳለም በዕለቱም ቢሆን ማከናወን ይችላል። ስለዚህ የመጀመሪያው ቅፅር ገብቶ መስቀል መሳለም፣ መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ .....ወዘተ ይቻላል
Oct 09, 2021