ታቃላቹ ህይወት ሳትሆን ክፉ ሰዎች ናቸው። ዛሬ የወደድኩት እና ብዙ ነገር ያደረኩለት ሰው ነገ እንደሚረሳኝ አላቅም። ግን እንደዛ ሆኗል። አሁን ልቤ አንድ ሺህ ቦታ ተሰንጥቋል። አው በእርግጥ ብዙ ችግሮች አሉብኝ። አንደኛው የጠረን ችግር ነው። በፊት እንደዛ አልነበርኩም አሁን ግን ከየት ይምጣ እንዴት ይምጣ ሰውነቴ ጠረን አለው። እናም እኔ ምፈልገው ጠንካራ መሆንን ነው። ሌሎች ስለሚያስቡት አለማሰብን ነው። ስለማልቀይረው ነገር አለመጨነቅ ነው ምፈልገው። ግን እንዴት ይሆናል አልቻልኩም። እባካችሁን በዚህ ጉዳይ ላይ መርዳት ከቻላችሁኝ ወይም የሚረዳ መፅሀፍም ካለ ግለፁልኝ። please እርዱኝ ማበድ ነው የቀረኝ።
Oct 08, 2021አእምሮህ በእውነታው አለም እና በሃሳብ አለም መካከል ያለውን ልዩነት አያውቀውም። ይህ ቀልድ ይመስላል አይደል? በህልምህ ቅዠት ውስጥ ስትገባ ምንድን ነው የሚፈጠረው? ከእንቅልፍህ ትባንናለህ… ልብህ በሃይል ይመታል… በላብ ተጠምቀሃል… በቃላት ለመግለጽ በሚያዳግት ሁኔታ ድንጋጤ ውስጥ ገብተሃል። ሆኖም ቅዠቱ በአእምሮህ ውስጥ ብቻ የነበረ ነው። በምንም አይነት አደጋ ውስጥ አልነበርክም… ሆኖም አእምሮህ ይህንን አያውቅም። ሰውነትህ ቅዠቱ የእውነት እንደሆነ አድርጎ ነው ምላሽን የሰጠው። በአንድ ወቅት፤ በበረዶ ላይ በመንሸራተት የሚታወቅ አንድ ስፖርተኛ (Skier) ላይ ተመራማሪዎች ጥናት አደረጉ። የዚህን ስፖርተኛ የሰውነት እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር መሳርያም በሰውነቱ ላይ ገጠሙለት። እናም ይህን ስፖርተኛ ከተራራ አናት ወደታች እየተንሸራተተ እንደሆነ እንዲያስብ ነገሩት። እናም በውጤቱ የእውነትም ከተራራ አናት እየወረደ እንደሆነ ሁሉ … የሰውነቱ ጡንቻዎች ተኮማተሩ። በእውነታው አለም እና በሃሳብ አለምም መሃል ያለውን ልዩነት አእምሮው አላወቅም። ይህም መሆኑ ለአንተ መልካም እና መጥፎ እድሎችን ይሰጣሃል። የፍርሃቶችህ፣ የመጥፎ ስሜቶችህ፣ የውድቀቶችህ ምንጭ ሃሳቦችህ ናቸው። አእምሮህ ከማንም በላይ አንተን ያምንሃል… አትችልም ካልከው… አዎ አልችልም ብሎ ይቀመጣል። ፈሪም ነህ ካልከው… መፍራትን ይጀምራል። የነገርከውን በሙሉ ያምንሃል። ሃሳቦችህ ለአእምሮህ መርዝ ይሆኑታል። በአእምሮህ ያመንከው ነገር እውነታህ ይሆናል።
Oct 09, 2021