በጣም ራሴን ለመለወጥ ሞከርኩ ሞከርኩ ግን አልቻልኩም ግን ከቀናት በኋላ ወይ ከሰዓታት በኋላ ምን ነበረ ለራሴ ያልኩት እላለሁ።አሁን ደሞ ገና አዲስ አመት ላይ ነን ጊዜውም አመቺ ነው። እና ይሆነ ነገር አደርጋለሁ ብዬ ባለማድረግ አንደኛ ነኝ motivated እሆንና ይሆነ ጊዜ ከዛ በቃ...እና አላማዬን እንድከተል እርዱኝ እውነት ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ነው ደሞ አንዴ አደለም ከሶስት ከአራት አመት በፊት ጀምሮ ማለት 😞እሱን ተዉት ዛሬ 2ፊልም አያለሁ ብዬ እራሱ ሳላይ ማለት😭እና tip ምናምን ከዚ በፊት እናተም አጋጥሞአችሁ ከሆነ እንዴት እንዳለፋችሁት።
Oct 08, 2021እኔም እንዳንተ በተለያዩ ነገሮች ለውጥ በራሴ ላይ ለማምጣት ትግሎችን አድርጌያለሁ ለምሳሌ የተለያዩ ሱሶችን እጠቀም ነበር በተለይ መጠጥ እና ሲጋራ ቢያንስ ለ 20 አመት ተጠቅሜያለው ከድራግም ከ መርፌ እስከ ፓውደሮች ድረስ እጠቀም ነበር። ለመተው እወስናለሁ ግን ከቀናት በውሀላ ያለማንም ቀስቃሽነት መልሼ እዛው ነበርኩ። በመጨረሻ ላይ ያደረኩት ለራሴ ማስታወሻ እንዲሆነኝ በጣቴ ላይ ቀለበት እና የማይሰራ ሰአት አሰርኩ። ለማጨስ ሳስብ ቀለበት እና ሰአቴን ሳይ አስታውሳለው። ይህ በቂ አልነበረም ከራሴ ጋር ረጅም ሰአት እከራከራለው። ተጨማሪም በየሳምንቱ ለማንም ሳላሳውቅ ለራሴ የትግል ውጤት ራሴን መሸለም ጀመርኩ ለምሳሌ ሳምንቱን ሳላጨስ ከቆየው እሁድን ሲኒማ በመሄድ ወይም አሪፍ ምሳ ራሴን ጋብዛለው። ይህንን ነገር ባህሪዬ እያደረኩት መጣው አሁን ላይ ድራግ ከወሰድኩ 4 አመታትን የአልኮልና ጫት 2 አመታትን ያለሲጋራ ደግሞ 8 ወራትን አሳልፌያለው። ቀለበቴ አሁንም አለች ሰአቴን ግን አስቀምጫለው። ሰዓቱ የቀን መቁጠረመያውን በራሴ ነበር የምቀይረው ካጨስኩ አንድቀን ወደውኃላ እመልሰዋለሁ። በዚህ መልኩ እቅዴን አሳካው አሁን ደግሞ ለስራዬ እጠቀምበታለው።
Oct 08, 2021