Guys does this site (https://oohmoney.xyz/991993806790560/) actually gives u money or is it scam answer if u experienced
May 19, 2020ሰሞኑን ከብዙ ሰዎች እየደረሱኝ ካሉ መልክቶች ውስጥ አንዳንድ ሰዎች የሚያቋቸውንም የማያቋቸውንም ሰዎች የሆነ ሊንክ በመላክ አንድ ዌብሳይት ላይ በመግባት ሬጅስተር ያድርጉ ብር ያስገኛል በማለት ከላይ በምስል ላይ ያለዉን ዌብሳይት እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ነው። ታዲያ የብዙ ሰዎች ጥያቄ ይህ ነገር እውነት ብር ያስገኛል ወይ የሚል ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ የይመዝገቡ ብር ያገኛሉ መልክት የደረሰኝ የዛሬ 3 አመት ገደማ ነበር። ሁሌም አንድ ዌብ ሳይት ስትከፍቱ መጀመሪያ ማድረግ ያለባችሁ ዌብሳይቱ ትክክለኛ ወይም safe ነው የሚለዉን ለማወቅ ብራውዘራችን ላይ ከ ሰርች ማድረጊያው አጠገብ ያለውን የቁልፍ ምልክት ከተጫንን በኋላ የዌብሳይቱን ምንነት ማወቅ ይቻላል። አስተማማኝ ዌብሳይት ከሆነ connection is secured ይለናል ካልሆነ ደሞ unsecured or unprotected conection የሚል ጽሁፍ ይመጣልናል። ይህ ብር ያስገኛል የተባለው ዌብሳይት የውሸት ወይንም ሃሰተኛ ኔትዎርክ ነው። አንድ ብር እንኳን አይከፍሏችሁም። 👉መጀመሪያ የማስታወቂያ ምስሎችን በማየት 150 ዶላር እንድትሰሩ ይነግራችኋል። 👉በመቀጠል ያን 150 ዶላር ለማውጣት በመጀመሪያ 40 ሰው መጋበዝ እንዳለባችሁ ያሳውቁና ሊንክ ይስጧችኋል። 👉 ነገር ግን 40 ሰው በናንተ ሊንክ ሬጅስተር ካደረገ በኋላ አካውንታችሁ ይቆፋል። ይባስ ብሎ እናንተን ብር ላኩ እንደ ማስያዣ ሊሏችሁ ይችላሉ። ⚠️ስለዚህ እንደዚህ አይነት ዌብሳይቶች ላይ ጊዜያችሁን ባታጠፉ መልካም ነው። ምን አልባትም አካውንታችሁ ወይንም ኢሜላችሁ ሃክ ሊደረግባችሁ ያችላል። በዌብ ሳይቱ ላይ የተቀመጡት የተለያዩ ሰዎች ያገኟቸው ብሮች ቁጥር ብቻ ናቸው። ዋጋ የላቸውም። እንደዚህ አይነት ዌብ ሳይቶች ብዙ ናቸው። አብዛኞቹ አንድ አይነት መልክ(layout) ፣ አንድ አይነት አሰራር እናም አንድ ባለቤት ነው ያላቸው። ምስሉ ላይ ካለው IVMoney .host ሌላ የሚከተሉት ተመሳሳይ ዌብሳይቶች አሉ። EKMoney .host OmMoney .PW IdMoney .PW YdMoney .WIN ObMoney .XYZ OZMoney .FUN AfMoney .ICU ከስማቸው ጭምር እንደምረዳው ሰዉን ለመሳብ ተብለው የተሰየሙ ናቸው። ስለዚህ በ እንደዚህ አይነት ዌብሳይቶች የራሳችንንም የሌሎችንም ጊዜ አናጥፋ። #Share በማድረግ ለሌሎችም እናስተላልፍ። 💧እጃችሁን በመታጠብ 🤝❌ባለመጨባበጥ 🏚ለአንገብጋቢ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ባለመውጣት 📿ፈጣሪን በመለመን እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከ ኮሮና ቫይረስ🦠 እንከላከል። #StaySafe #InfoHub
May 19, 2020