Hello, am an ortodox gin i have some gira megabats , why do we need mamaledat the 1st place. lemin dinewu emebetachin, melaikt,or tsadqan milja yasfelegewu why dont we just ask God what we need, i know it is silly question but please answer for me🙏🏾🙏🏾🙏🏾
Oct 07, 2021ሳይኾን ባለሟልነታቸው ባሰጣቸው ጸጋና ክብር ተጠቅመው ነው (ማቴ. ፲፭፥፳፩-፳፰)፡፡ እኛም ከቅዱሳን ኋላ ኾነን ብንጮኽ ይህንኑ ነው የሚያደርጉልን፡፡ ሦስተኛ እግዚአብሔር በአማላጁና በሚማለድለት መሃል ገብቶ ሲያዝ የሚፈጸም የምልጃ ዓይነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በቀጥታ ምሕረት መስጠት እየቻለ ‹‹እገሌ ይጸልይልህ›› ብሎ ኀጥኡን መላኩ ስለ ምን ነው ቢሉ የቅዱሳንን ክብርና ባለሟልነት ለመግለጽ ስለ ወደደ ነው፡፡ አንድም እንዲህ ያለውን የመዳኛ መንገድ ማብዛቱ የቸርነቱ ውጤት ነው፡፡ ይህን ለማየት ምሳሌ የሚኾነን ደግሞ የአብርሃም ታሪክ ነው፡፡ የጌራራው ንጉሥ አቤሜሌክ የአብርሃምን ሚስት ከክብር ሊያሳንሳት በወሰዳት ጊዜ የኀጥኡን መጥፋት ሳይኾን ከጥፋቱ ተመልሶ በሕይወት መኖሩን የሚወድ አምላክ ‹‹የሰውየውን (የአብርሃምን) ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና ስለ አንተም ይጸልያል ትድናለህም፤›› ብሎ ሲራራና ኀጥኡን ወደ ጻድቁ ሲመራው እንመለከታለን (ዘፍ. ፳፥፩-፲፰)፡፡ ፬. ምልጃ በዐፀደ ነፍስ ‹‹በዐፀደ ሥጋ ያለውን ምልጃ እንቀበላለን፤ በዐፀደ ነፍስ ግን አይደረግም›› ለሚሉ መጽሐፍ ቅዱስ በዐፀደ ነፍስ ስላለው ምልጃ እንደሚከተለው ያስተምረናል፤ ነፍስ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ተመልሳም ወደ እግዚአብሔር የምትሔድ፤ እንድናስብ እንድንናገርና ሕያው ኾነን እንድንኖር ያስቻለችን ረቂቅ ፍጥረት ነች (ዘፍ. ፪፥፯፤ መክ. ፲፪፥፯)፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ዂሉን የሚያውቁት፣ ከሞት (የሥጋ ሞት) በኋላ ሕያው የሚኾኑት፣ የምናናግራቸውና የሚያናግሩን በዚህች ነፍስ ነው፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የሙታን ሳይኾን የሕያዋን አምላክ መኾኑን የነገረን ለዚሁ ነው (ማቴ. ፳፪፥፴፪)፡፡ ወደ እግዚአብሔር የሔዱ ቅዱሳን ከዚህ ዓለም ዕረፍታቸው በኋላ በዚህ ዓለም ስለሚኾነው ነገር እግዚአብሔር በገለጠላቸው መጠን እንደሚያውቁ እና እንደሚያማልዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች እንመልከት፤ ሀ. ከዚህ ዓለም ከተለየ (ከክርስቶስ ልደት በፊት) አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ገደማ የሚኾነው ነቢዩ ሙሴ እና ነፍሱና ሥጋው ሳይለያዩ በብሔረ ሕያዋን የሚኖረው ነቢዩ ኤልያስ ሁለቱም በዘመነ ሥጋዌ ከጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በደብረ ታቦር ተገልጠዋል፡፡ ‹‹ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ኾነ። እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሉቃ. ፱፥፳፱-፴፪)፡፡ ለ. ቅዱሳን ሰማዕታት ካረፉ በኋላ በዐፀደ ነፍስ ኾነው በዚህ ዓለም ስላለው ኹኔታ እንደሚያውቁና እንደሚጸልዩ በራእየ ዮሐንስ እንደሚከተለው ተገልጧል፤ ‹‹አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ‹ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?› አሉ። ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፡፡ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው፤›› (ራእ. ፮፥፱- ፲፩)፡፡ ሐ. ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው የአብርሃም የባለጸጋው እና የአልዓዛር ታሪክ በአካለ ነፍስ ምልጃና ልመና መኖሩን የሚያስረዳ ነው (ሉቃ. ፲፮፥፲፱)፡፡ መ. ቅዱስ ጴጥሮስ ከሞቱ በኋላ ለምእመናን እንደሚጸልይላቸው የገለጠው ሌላው ምስክር ነው፡፡ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲኾን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ፤›› በማለት ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው (፪ኛ ጴጥ. ፩፥፲፫-፲፭)፡፡ ማጠቃለያ በሥጋ የተለዩ፣ በነፍስ ግን ሕያዋን የኾኑ ቅዱሳን በሥጋ ለሞቱት ሰዎች ያማልዳሉ፤ በሥጋ ያልሞቱት ደግሞ በሥጋ ለሞቱት ‹‹አማልዱን›› እያሉ ይጸልያሉ፡፡ ‹‹በዚያ ወራት የወዳጆቼ የጻድቃን ልመናቸው ወደ ሰማይ ወጣች፤ ከዚህ ዓለም በግፍ የፈሰሰ የጻድቁም ደም በመላእክት ጌታ ፊት ተወደደ፡፡ በእነዚህ ወራቶች በሰማይ የሚኖሩ ጻድቃን በአንድ ቃል ኾነው ተባብረው ያመሰግናሉ፤ ለሰው ፈጽመው ይለምናሉ፡፡ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሄኖክ ፲፪፥፴፫)፡፡ ሙታን ለሕያዋን፣ ሕያዋን ለሙታን ይጸልያሉ ማለትም ይኸው ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ይጠብቀን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Oct 07, 2021