#Health ሰላም እንዴት ናችሁ? የጆሮዬ የመስማት አቅም በየጊዜው እየቀነሰ አስቸገረኝ። ከሰዎች ጋር ለማውራት ተቸግሬአለሁ፤የጀመረኝ ብዙ ጊዜው ቢሆንም በየቀኑ እየባሰኝ መቷል። ወደ ህክምና ለመሄድ ደግሞ ምንም ገንዘብ የለኝም፣ለጊዜው ተመርቄ ስራ እየፈለከሐ ነው። እባካችሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሩኝ! Hi guys! My hearing is constantly being impaired time to time. I'm unable to hear easily.I find it difficult to talk to people; I don't have any money to go to the doctor, I'm just looking for a job after graduation. Please tell me what to do!
Oct 05, 2021እሱ ነገር በማውቃቸው ሁለት ሰዎች ላይ ተከስቶ ነበር እናም ጆሮአቸውን ማሳጠብ ነበር መፍትሄው። ማሳጠብ ሲባል በውሃ አይደለም። በተፈጥሮ የሰው ጆሮ ኩክ የማስወገድ ስርአት ያካሂዳል። ነገር ግን ሁሉም ጆሮ አይደለም። ችግሩ የጆሮ ኩክ ከመተን በላይ ታምቡራችን ላይ መከማቸቱ ነው። ፒያሳ ወደ እሳት አደጋ የሚወስደው መንገድ አካባቢ የጆሮ ህክምና ሚሰጡ ተቋማት አሉ። ዋጋቸውም ውድ አይደለም። ደህና እንደምትሆን ተስፋ አለኝ።
Oct 05, 2021