ሰላም ሰዎች እእእ እንዴት እንደምል አላውቅም ግን እስኪ ምከሩኝ እድሜዬ 17 ነው ድሮ የአብነት ተማሪ ነበርኩ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ አስቀዳሽ እና ብዙ ሰው እኔ የቤተክርስቲያን ልጅ እንደሆኑክ ያስባሉ ፣ ግን እኔ እራሴን አርክሻለው በ ግለ ወሲብ ሱሰኛ ሆኛለው ጠዋት ፀሎት ላደርግ ሳስብ ማታ ላይ ግለ ወሲብ ያስፈፅመኛል እራሴን ከ አብነት ትምህርት አራቅሁ የ ህይወት ህልሜን አጣውንት ዲያቆን ሆኜ ማገልገል እመኝ ነበር ግን ተሰናከልኩ.. ፀበል ስጠመቅ አንድ ቀን ሳያሳስበኝ ይውላል ስተው መጠመቄን እንደገና ያሳስተኛል ፀሎት ማቋረጥ አልፈልግም ግን አንዳንድ ሰዎች ግለ ወሲብ ከፈፀምክ ፀሎት መፅሀፍ ይዘክ መፀለይ አይቻሉም ስላሉኝ ብዙውን ጊዜ አልፀልይም መመለስ እፈልጋለው ግን የሆነ ነገር ይይዘኛል ተመልሼ እራሴን ከዚህ ነገር አንፅቼ ስጋ ወደሙን ለመቀበል እንዲያበቃኝ እፈልጋለው የተዋህዶ ልጆች በፀሎታቹ አስቡኝ እና እባካቹህ ወደ ድሮ ማንነቴ እንድመለስ እርዱኝ 🙏🙏🙏
Oct 04, 2021ወንድሜ አይዞህ እግዚአብሔር ከዚህ ሕይወት ያወጣሃል። ዲያቆን የመሆን ህልምህም የከሸፈ አይደለም የፈጸምከው ግለ ወሲብ ብቻ ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነውና ይቅር ይልሃል። ከዚህ ህይወች ብቸኛ የመውጫ መንገዱ ደግሞ ንስሐ ብቻ ነው። ጨከን ብለህ ንስሐ ግባ፤ ስጋ ወደሙንም ተቀበል። ከአብነት ትምህርትህም ተመለስ ወንድሜ እግዚአብሔር ቸር ነውና ዲቁናህንም ይሰጥሃል። ንስመ ከገባህና ስጋ ወደሙን ከተቀበልክም በኋላ በጸሎት ወደዚያ ሕይወት እንዳትመለስ እግዚአብሔርን ጠይቀው። እኛ በራሳችን ደካማ ነንና። አይዞህ ወንድሜ እግዚአብሔር ይርዳህ። ድንግል ማርያም አትለይህ
Oct 05, 2021