ዛሬም እንፈላሰፍ። የእኛ ህልውና!!! እቺን አለም እግዚአብሔር ፈጠረ እንበል። የፈጠረው ደግሞ በቃሉ ነው። ይህ ማለት ከባዶ ነገር አንድ ግዙፍ የሆነ አለም በቃሉ ፈጠረ። እዚ ጋር ቃል የሚለውን ቃል አስተውሉ። ከዛ በዛ ቃል የፈጠረው አለምን ተጠቅሞ ደግሞ የሰው ልጅ ፈጠረ። ይህ ማለት እኛ የእግዚአብሔር ቃል የቃሉም እጅ ፍጥረት ከሆንን። ቃል ደግሞ የሚመጣው ከእሳቤ ከሆነ ፥ ይህ አለም የመጣው ደግሞ ከቃል ሲሆን ፥ እኛ ማለት እሳቤ እንጂ በእውነተኛው አለም የለንም ማለት ነው። ይህ ማለት የሰውም ልጅ ሆነ በዚ አለም አለ የተባለ ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር እሳቤ ውስጥ ያለ ነገር እንጂ በእውነታው አለም ላይ ኖሮ አይደለም። በዚ ላይ የተለየ ሀሳብ አላቹ? እስቲ አስረዱኝ። የኔ ሃሳብ! ለኔ ግን ይህ አለም በራሱ የኖረ መጀመሪያም መጨረሻም የሌለው ግዑዝ ነገር ነው። ግን በዚውስጥ ጥሩና መጥፎ መንፈስ አብሮት ተገኘ።
Oct 04, 2021ፈጣሪ ባይኖር እውነታ የሚባል ነገር ራሱ ከየት ይመጣል ወንድማችን (እ/ውነትን ከ ውሸት መለየት የቻልከው በራሱ እኮ ፈጣሪ ስላለ ነው ) ሶ በድጋሚ እልሃለው ከፈጣሪህ ጋር ጭንቅላት አትለካካ { ኢትስ አባቭ ዩር ፔይ ግሬድ ይላሉ ውጪዎች }😊 ባቅምህ ባለ ነገር ላይ ተፈላሰፍ ስትፈላሰፍ ብዙ የሚያፈላስፉ የኑሮ ጉፋያና ድሪቶዎች አሉ እነሱ ላይ ተፈላሰፍ መጀመሪያ 😉
Oct 05, 2021