ሠላም ቤተሠብ እንዴት ናችሁ? በስራ የአንድ ተቋም ባልደረቦች ነን ትውውቃችንም ተቋሙ ውስጥ ሲሆን ላለፈው 1 አመት ፍቅረኛዬ ነበረች ነገር ግን በት/ት አማካኝነት ተራርቀናል በእኔ ግፊት አልፎ አልፎ እንገናኝ ነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሆነ ነገር ተጋጨን ይቅርታ ብላት እምቢ ብላ "ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋ ነው የምቀጥል እዳትደውል" ስትል ተናድጄ ሳምንት እንደዘጋኃት እራሷ ደውላ አንተ አኩራፊ ለምን ዘጋሃኝ አለችኝ እና እንደገና መደዋወል ጀመረን 2 ሳምንት እንዳወራን በድጋሜ ዘጋችኝ ምነው ስል ይቅር እንዳላለችኝ ስትነግረኝ 2 ቀን ዘጋዋት በዚህ መኃል የድሮ ጀለሷ ሁለቱ ሳያውቁ ስልኩ ነበረኝ እና ቴሌግራም ላይ ሰርች አድርጌ ስመለከት በተዘጋጋንባት ሁለት ቀን ውስጥ ሁለቴ ፕሮፋይል ቀየረ ሁለቱም ተቃቅፈው የሚያሳይ የቅርብ ጊዜ ፎቶ ነው እሷ ግን ይሄን እንደማይ አታውቅም የሷ ፕሮፋይልም አልቀየረችም እሷ ደግሞ 2ኛው ቀን ጀምራ በድጋሜ መደወል ጀምራለች እኔ ግን ፎቶውን ካየሁ በኃላ ተሰፋ ቆርጬ አላነሳም ፎቶውን ባየሁት ቁጥር ግን ሀይማኖቴ ባይፈቅድም ልበቀላት እያሰብኩ ነው ምን ትመክሩኛላችሁ???
Oct 04, 2021የምን መበቀል ምናምን ነው ብሮ? ጀስት ጠይቃት የምር ካንተጋ መሆን ሀፈለገች ፈለገች ሁሉንም ተውና ፍቅራችሁን ቀጥሉ፡ አልያ ደግሞ በሰላም ተለያዩ። እናንተ ትልልቅ ሰዎች አይደላቹ እንዴ የምን በቀል ምናምን ነው ጎበዝ
Oct 04, 2021