እንኳን አደረሳችሁ !!!!!!! የኔ ጥያቄ 1) ኢሬቻ መከበር የተጀመረው መቼ ነው? 2) ሁለተኛው የሚከበረው መቼ ነው? ምክኒያቱስ ምንድን ነው? ለምን እንደ መስከረሙ በድምቀት አይከበርም? 3) ደብረዘይት ና አዲስ አበባ እንዴት ተመረጡ በምን መስፈርት በኦሮሚያ እኮ ሆራ አርሰዲን የሚበልጡ ትላልቅ ሀይቆች የሉም እንዴ? በሌላ ነገር ሳትተረጉም ብትነግሩኝ በጣም ደስ ይለኛል ግራ ስለገባኝ ነው
Oct 02, 20211) እስካሁን ተጀመረበት የሚባል ጊዜው በውል አልታወቀም። 2) 2ኛው የሚከበረው በጸደይ መግቢያ በውርኃ የካቲት ነው። ምክንያቱ ደሞ በባለፈው በጋ ለተሰበሰበው ሰብል አመስግነው ለመጪው ወር ደሞ መሬቱን በዝናብ እንዲያረሰርስ እጽዋቱንም እንዲያለመልም ይለመናል። እንደ መስከረሙ በድምቀት የማይከበርበት ምክንያት ደሞ እንድ ብዙ ስላልተለመደና እና የሥራ ገበታ ክፍት በሆነበት ሰዓት በመሆኑ 3) የሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው ከሁሉም ቀዳሚ እና የመጀመርያው ስለሆነ ነው። የቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ግን መከበር የጀመረው ቅርብ ከሁለት ዓሥርት ዓመታት በፊት የመነመነውን የኢሬቻን በዓል ለመመለስ በተደረገው ጥረት ነው፥ አርሰዲም የሰውዬው ስም ነው። ከሁለቱም ከሁሉን በልጦ እንዲከበር ያረገው ግን የቱለማ ኢሬቻ በመሆኑ ነው። ቱለማ ከኦሮሞ ነገዶች ታላቁ ነው፥ ታላቅ ወንድም ደሞ ቤተሰቦቹን ከሁሉም አቅጣጫ ይሰበስባል። ይህ ነው ምክንያቱ
Oct 02, 2021