ለተጋሩዎች የትግራይ ሚድያዎችእንዲያው ተሳስተው ድንገት እንኳ በትግራይ ስላለው ራብ እና ጥም ስለተከሰተው ጠኔና ችጋርም አያወሩም! በዳያስጶራ ያለው ትግሬም "በሎም" በሚለው በአሉላ ሶሎሞን የፌስ ቡክ ጥቅስ ራሱን "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ" ከንቱ ስሜት ሲቃትት ከመዋል በቀር ቆም ብሎ ለማሰብ ለምን አይፈልግም? ስለ ድል፣ ስለ ተቆጣጠርነው ወሬ እንጂ እንደቅጠል እየረገፉ ስላሉ ምስኪን የትግሬ ወጣቶች ለምንስ አይተነፍሱም? እሱኛው ለምንስ ግድም ሲሰጣቸው አይታይም? ትግሬዎቹ በየትኛውም የሚድያ መርሀ ግብራቸው ላይ ስለ ችግራቸው፣ ስለ ራብ ጠኔአቸው፣ ስለ መብራት ስልክ መጥፋት እና እጥረቱ እንብዛም ለምን አይተነፍሱም? እሱኛውን ችግራቸውን ሌላው ኢትዮጵያዊ እና የፈረንጅ ጋዜጠኞች፣ የአውሮጳና የአማሪካ ባለሥልጣናት እንዲጮሁላቸውስ ለምንድነው የሚፈልጉት? እነሱ ስለ መከራው፣ ስለ ሰቆቃው ትንፍሽ ማለት ሳይፈልጉ ስለ ምርኮ፣ ስለ አሸናፊነት፣ ስለ ድል፣ ስለ በሎም ብቻ ነው እየደሰኮሩ ሰቆቃቸውን ግን ሌላው እንዲያወራላቸው ለምን ይፈልጋሉ? ሰንጋ እየቀረበለት የሚዋጋን ልምድ ያለው ወታደር የማሽላ ቆሎ እየበሉ እገጥማለሁ ማለትስ ምን ይሉታል? ለጥቂት 50 ዓመት ሙሉ ከሥልጣን መውረድ ለማይፈልጉ ጥቂት ፊውዳል የህወሓት ባለ ሥልጣናት ተብሎ ምስኪኑ ትግሬ እንደ ቅጠል በዐማራና በአፋር ምድር መርገፍ አለበትስ ወይ??
Sep 28, 2021መጀመሪያ ያሉቱን 2ቱ ሚድያዎች በተቻላቸው አቅም በ ትግራይ ያለው ችግር እያወጡ ነው። አላየሁም ማለት መብትህ ነው። ሁለተኛው በሎም የሚለው መከላከያ ሲቀጠቀጥ እና ምን ይበል። ይህ በዚህ 3 ቀን እንኳ አፋር ላይ የነበረው ጦሩነት ማየት ትችላለህ (አፋር ዘመድ ካለህ ደውለህ ጠይቅ)። ሶስተኛው ሰንጋ እየበላ ያለው መከላከያ እንዴት ቆሎ በልቶ መዋጋት ይችላል ያልከው ሰንጋ በልቶ ምን የተለየ ተኣምር ሲሰራ አይተክ ነው። አማራ ክልል እነኳ ነፃ ማውጣት ኣቅቶታል የትግራ ሰራዊት ከባህርዳር >100 ኪ.ሜትር ከጎንደር>120 ኪ.ሜትር ርቀት ሁኖ እሱን መሰባረር እንኳ አለቻለም። እና ምን ማለት ፈልጌ ነው ኣላማ እንጂ ሆድ ታሪክ ኣይቀይርም። ከዚህ ሁሉ ግን "ሰላም ይሻላል" በሁለቱም በኩል የሰው ሂወት እየጠፋ ነውና።
Sep 29, 2021