What makes cerebrating ireecha here in Addis soo special? I got no problem with it, just wanna know.
Sep 26, 2021ከሌሎቹ የተለየ ያረገው በሁሉም ቦታ ከሚደረገው ኢሬቻ/ኢሬሳ/ዺባዩ (በሌሎች ቦታ የሚጠራበት ስም ነው) በዓላት ኦሪጂናል እንደመሆኑ ነው። ከክፍለዘመናት በፊት የኦሮሞ ህዝብ አስተዳደር በአንድ ጨፌ ሥር በነበረበት ዘመን ማዕከል ስለነበረ ነው። ማለትም ከሁሉም ጫፍ የነበሩት ሰዎች መሃል ከተማ በመምጣት በሆራ ፊንፊኔ ተሰባስበው እሬቻን ካከበሩ በኋላ መመለስ ያለባቸው ከተመለሱ በኋላ እድሜ ብስሎቹ ደሞ ወደ ኦዳ ነቤ (ዱከም) በመሄድ የጨፌ ጉባኤ አድርገው ወደ መጡበት ይመለሳሉ። ይህ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ በመምጣቱ ኦዳ ነቤ ለእድሜ ታላቁ ለቱለማ ነገድ ተሰጥቶ ሌላ 4 ኦዳ በመጨመር 5 ጨፌ፣ 5 ኢሬቻ ተደረገ፥ እሱም ሲከብድ 10 ተድረገ። ስለዚህ የሆራ ፊንፊኔን ለየት የሚያረገው የጥንት የጠዋቱ በመሆኑ ነው።
Sep 26, 2021