#relationships ከተወሰኑ አመታት በፊት ፍቅረኛ ይዤ ነበር ለ6 አመታት አብረን ቆይተናል። ግን ባሳለፍነው ጊዜ ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ ፈተናዎችን ተፈትኜባታለው። በኔ ላይ ያልሰራችው ግፍ የለም ቢሆንም ግን በሰላም ተለያየን። አሁን ከተለያየን 5 አመታትን አስቆጥረናል ግን ከሷ በውሀላ ነገሮች ሁሉ ከባድ ሆነውብኛል። በሞያዬ ከግብርና - Biotechnology ድረስ እሰራለው ግን ትዳር ቀርቶ የፍቅር ግንኙነት መጀመር አልቻልኩም። ብዙ እህቶችን እቀርባለው የፍቅር ጥያቄዎችም ይመጣሉ። ከህትነት እንዲያልፉ ግን ፈቅጄ አላውቅም፤ ምን ይሻለኛል? እድሜያም 32 ነው? ወደ ፍቅር ህይወት መግባትና ቤተሰብ መመስረት እፈልጋለው፤ ግን እንዴት ላድርግ?
Sep 26, 2021ከአንተ ጋር በጣም ተመሳሳይ ነገር ገጥሞኝ ስለሚያቅ ሁለት ነገር ብቻ ልበልህ 1.በእንደዚህ አይነት የህይወት ምዕራፍ ላይ መቀመጥህ ያሳዝናል ብዙ ሰው ጥሮ ግሮ ተምሮ ስራ ይዞ ወደ ትዳር አለሙ ሲገባ ተግዳሮት የሚጋፈጠው ቁጥሩ ቀላል አደለም አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች በስራ ወይም በትምህርት አለም ላይ እንደነበሩት በፍቅር ወይም በትዳር አለም ውስጥ ሲገቡ የተለየና አስቸጋሪ ባህሪ ይዘው መምጣታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።አንተም ከነዚህ አይነት ወንዶች ውስጥ ገፈት ቀማሽ በመሆንህ የምር በጣም አዝኛለሁ። 2.ችግር የፍልስፍና እናት ነች ይባላል እንደ እድል ሆኖ አስቸጋሪ ከምትባል ሴት ጋ ህይወት አገናኝቶህ ነበር።በእርግጥ አንደኛው የኑሮ ገፅህ ላይ ጥቁር ነጥብ በማሳረፏ ቀጥይ የፍቅር ህይወትህም ሆነ ከሴቶች ጋር ያለህን ግንኙነት ወደ ፍቅር ብሎም ጋብቻ እንዳትቀይር አይምሮ አግዶህ ይሆናል ነገር ግን ያልገደለህ ችግር ያጠነክርሀል ነውና ሰፋ ያለ ጊዜ ሰጥተህ ካለፈው ነገር ጥሩ ትምህርት ውሰድ አብራቹ ባሳለፋችሁት አመታት የነበሩትን ጥሩና መጥፎ ነገሮች ነቅሰህ ለይ ለጎዱን ሰዎች ትልቁ በቀል በኛ ስኬት ከነሱ ልቀን መገኘት ነው ስለዚህ እሱን ስትጨርስህ ራስህን ለአዲስ የህይወት ምዕራፍ አዘጋጅ ያለፈውን ስህተት ላለመድገም ሞክር ችግርህ እሚያቆምህ ሳይሆን አንድ ደረጃ ከፍ እንዲያረግህ ይሁን ጥሩ ጓደኞች ፍጠር ከነሱም ተማከር መፅሀፍት አንብብ!! መልካም ጊዜ ይሁንልህ
Sep 26, 2021