Hi, sewoch Esiti yemesikelin, ye dameran tirigum kulich adirigo minegeregn. 🙏
Sep 25, 2021✍✍✍✍ተጨማሪ ግንዛቤ✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ #ደመራ_ለምን_ይከበራል?#ትውፊቱስ_ምንድነው? 👉 ደመራ፣ ደመረ ጨመረ ካለው የግእዝ ቃል የመጣ ነው ትርጉሙ መጨመር (መከመር) ማለት ነው፡፡ ኦሪታውያን ከመስከረም ፲፭-፳፪ ለስምንት ዕለታት በዓለ መጸለትን ያከብሩ ነበር፡፡(ዘሌ.፳፫፥፮) በዓሉን የሚያከብሩት በብዙ መንገድ ሲሆን፤ እንጨት እየሰበሰቡና እየከመሩ ማታ ማታ በእሳት እያቃጠሉ በመጫወት ያከብሩታል፡፡ ኋላ ግን ተሻሽሎ የእሳት ማንደጃ ቀን በመስከረም ፲፯ ላይ ቆሞአል፡፡ ያም በዓል ከዘመነ ሐዲስ ሲደርስ የመስቀል ደመራ ተብሎ ተሰይሟል፡፡ 👉 ደመራ የማብራት ሥርዓት መቼ ተጀመረ? ለምን? 1— የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ከቁስጥንጥያ ተነሥታ ድሆች ክርስቲያኖችን ለመርዳትና አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራት በ፫፻፳፮ ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች፡፡ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ የጌታች መስቀል ተአምራት እንዳያደርግ አይሁዶች በምቀኝነት ቀብረውት ነበርና የተቀበረበትን ቦታ የሚያሳያት አጥታ በመፈለግ ብዙ ጊዜ አሳለፈች በኋላ ግን አንድ ኪራኮስ የሚባል እስራኤላዊ አካባቢውን ነግሯት ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ ብትማጸን የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ አመለከተ፡፡ እርሷም በምልክቱ መሰረት ብታስቆፍር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኘች፡፡ የእርሱ መስቀል ለመሆኑ ድውያንን በመፈወሱ፣ አንካሳ በማበርታቱ፣ ጎባጣ በማቅናቱ ታውቋል፡፡ ይኽንንም ይዞ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሰገደ ጢስ ብሎ በድጓው ጽፎት ይገኛል (የዮሐንስ ድጓ)፡፡ ስለዚህ በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒ አብነት በማድረግ ነው፡፡ 2— በተጨማሪም ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ባገኘች ጊዜ የደስታዋን መልእክት ለልጇ እንዲደርሰው ለማድረግ እንዳሁኑ ዘመን ስልክና ሬድዮ ስላልነበር በዚያን ጊዜ መልእክትን ሩቅ ሥፍራ ለማስተላለፍ ሲፈልጉ በየተራራው ቃፊሮችን (መልእክተኞችን) መድበው መልእክቱ ከሚተላለፍበት አቅራቢያ ተራራ ላይ ያለው ቃፊር (መልእክተኛ) ችቦ በማብራት ከርሱ በኋላ ባለው ተራራ ላይ ላለው ቃፊር ምልክትን በማሳየት መልእክቱን ያስተላልፋል ሌላኛውም ቃፊር ችቦን እያበራ ለሌላኛው መልእክተኛ ምልክትን በመስጠት በዚህ መልኩ ያስተላልፋ ነበር፡፡ ንግሥት ዕሌኒም ይህንን ዘዴ በመጠቀም የመስቀሉ መገኘት ወሬ (የምሥራች ዜና) ቁስጥንጥንያ እንዲደርስ አደረገች ልጇ ቆስጠንጢኖስም መልእክቱ እንደ ደረሰው ወደ ኢየሩሳሌም ሂዶ እናቱን አግኝቶ ብዙ ስጦታ አበርክቶላታል እርስዋም መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት 10 ዕለት ቅዱስ መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች የደመራ ማብራት ሥርዓት ከዚህ ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ የበረከት በዓል ያድርግልን፡፡ አሜን!!! 🙏🙏🙏
Sep 26, 2021