እስከ ዓለም ፍፃሜ ምድርን የከበቧት ዘንዶዎች (የአራዊት ንጉሦች) ሌዋታን በባህር በስተግራ በኩል የተጋደመችው እንስት ነች። ብሔሞት በየብስ በስተቀኝ በኩል ተጋድሞ ምድርን የከበበ ተባዕት ነው። ሁለቱም ዘንዶ መሳይ ፍጥረታት ክብ ሰርተው በጅራታቸው ተቆላልፈው በአፋቸው በኩል የተፋጠጡ ሲሆን...የተገናኙ ዕለት ዓለም ፍፃሜዋ ይሆናል ተብሎ ይነገራል። ይህም ንግርት በኛ ጥንታዊ ሰነዶች ብቻ ሳይሆን በጥንታዊ ምዕራባውያን፣በህንድና በአረብ ታሪኮች ውሥጥ ተፅፎና በስዕል ተገል ይገኛል። የሰው ልጅ የሚኖርበት ምድር ለ ፯ የተከፈለ ሲሆን ፩_ብሔሞት ፪_ሌዋታን ፫_የአራዊት መኖሪያ ፬_በርባኖስ ፭_እሳት ፮_በረዶ ፯_የሰው ልጅ መኖሪያ በሚል። ብሔሞትና ሌዋታንም የኛን ምድር ፯ኛውን ክፍል የሰው መኖሪያ እንደ መቀነት ተጠምጥመው ይዘዋት ይገኛሉ። አመጋገባቸው # በፀጉራቸው ሲሆን... ብሔሞት የየብስ ፍጥረታትን (በድን) ከሰው በስተቀር በፀጉሩ በኩል ይመገባል። ሌዋታን የባህር ፍጥረታት (በድን) በፀጉሯ በኩል እየተመገበች ትኖራለች። ስለ # አኗኗሯቸውና ምን # ይመስላሉ የሚለውን እንደነ ሄኖክ፣ዘርዓ ብሩክ፣ዕዝራ ሱቱኤል፣ገድለ ዑራኤል፣የመሪራስ አማን በላይ መፅሐፍና አክሲማሮስ የተባለው የፍጥረታት መፅሐፍ ላይም ተገልፆ ይገኛል። ዓለም ሲፈጠር የተፈጠሩ የሐሙስ ፍጥረታት ናቸው። አፍ'ለአፍ የገጠሙ ዕለት ተፍፃሜተ አለም እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ።
Sep 24, 2021