#health
ሰላም፤ የመልቲፕል ስክለሮሲስ(MS) ህመም ተጠቂ ነኝ,እንደ እኔ ያሉትን ኢትዮጲያዊ የ MS ተጠቂዎችን እንደ ቴሌግራም እና ፌስቡክን በመጠቀም "MS in Ethiopia" በሚል ገፅ የተወሰኑ የ MS ተጠቂዎችን በማድረግ ህጋዊ ፋቃድ ያለው ማህበር መስርተናል፤በአለም አቀፍ ደረጃ ለህመሙ ፍቱን መድሀኒት ባይገኝለትም በሽታው አካል ላይ የበለጠ ጥቃት እንዳያደርስ የሚሰጡ መድሀኒቶች አሉ፣እኔ በማውቀው እኒህ መድሀኒቶች እዚህ አገራችን የሉም ፤ ከሌላ ሀገር ለማስመጣትም በጣም ውድ ናቸው ፤ማህበር ከመሰረትንም አመት ይሆነናል እስከአሁን ድጋፍ የሚያረግልን አካል አላገኘንም፤ከመንግስትም ይሁን ከሌላ አካል እንዴት ድጋፍ እናገኛለን?
Sep 20, 20213 engagements