ይህን ጥያቄ ዲያቆን ሄኖክ አብራርቶ ሲመልስ ነበር። የቱጋ እንደኾነ ረሳሁት። 😭
Sep 15, 2021ይህን ጥያቄ ዲያቆን ሄኖክ አብራርቶ ሲመልስ ነበር። የቱጋ እንደኾነ ረሳሁት። 😭
Sep 15, 2021Ere tetemkual besefiw mabrariya kefelegsh demo ye ephratus wenz yemilew metshaf lay ke 136-137 anbbiw
Sep 15, 2021ሳይጠመቅ አጥምቋል ብዬ አላስብም guess new no evidence
Sep 15, 2021በቤተክርስቲያን ሦስት ዓይነት ጥምቀት አለ። #1የልጅነት ጥምቀት(ይህ ጥምቀት የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት ከአብራከ መንፈስቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ስመ እግዚአብሔር ተጠርቶ ውሃው ወደ ማየ ገቦነት በመቀየር ማለትም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ላይ ሳለ ሌንጊኖስ በተባለ አይሁዳዊ ወታደር ጎኑን ሲወጋ በ ለ ቅርጽ ውሃና ደም ፈሷል።ወንድ በ40 ሴት በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት ለማግኘት ሲጠመቁ የሚጠመቁበት ውሃ በአጥማቂው ካህን ጸሎት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጎን ወደ ፈሰሰው ውሃነት በመቀየር ከውሃና ከመንፈስ ይወለዳሉ። ዮሐ3÷5-15 #2የፈውስ ጥምቀት(ይህ ደግሞ ከስጋዊም ሆነ ከመንፈሳዊ ደዌ ለመላቀቅ እግዚአብሔር ራሱ ካዘጋጀው ቅዱስ ስፍራ በሚፈልቅ ጸበል ይፈፀማል።ዮሐ5÷4 ዮሐ9÷11 #3ቄደር ጥምቀት(ሃይማኖታቸውን ክደው ለተመለሱ፣ለጣዖት የተሰዋውን ለበሉ፣ከአህዛብ ጋር በዝሙት ለወደቁ ሰዎች ከሀጢያት መንፅያ ይሆን ዘንድ ይፈፀማ። ዮሐንስ ጥምቀት ግን ከእነዚህ ሁሉ ትለያለች። እርሱ ጸያሔ ፍኖት(መንገድ ጠራጊ)እንደመሆኑ ያመኑትንም ያላመኑትንም ``ነስሁ ወእመኑ እስመ ቀርበት ይእቲ መንግስት ሰማያት ''እያለ የንስሐ ጥምቀትን ነበር ሚያጠምቀው። ወደ ጥይቄው ስንመለር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተጠምቋል ወይ?? አዎን ተጠምቋል። በቤተክርስቲያናችን የልጅነትን ጥምቀት ሳያገኙ ነገር ግን በሰማዕትነት ላለፉ ሰዎች ክርስቶስ የደም ጥምቀት እንደሚያጠምቃቸው ታስተምሰናለች።ለምሳሌ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘመን ክርሰቲያን ያልነበሩ ሰዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ አምነናል እያሉ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።ይህም በቤተክርስቲያን የደም ጥምቀት ይባላል።መምህር ወ መገሰጽ የነበረው መለኮትን ያጠመቀው ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድምህን ሚስት ታገባ ዘንድ ላንተ አልተፈቀደልህም ብሎ ስለገሰጸው እና ለእግዚአብሔር ሕግ ቀናኢ ስለ ነበር ንጉሥ ሄሮድስ መከራን አጽንቶበታል ከዚያም በኋላ አንገቱን በሠይፍ አስመትሮታል። በዚህም የተነሳ ቅዱስ ዮሐንስ የደም ጥምቀትን ተጠምቋል።
Sep 15, 2021መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የለም። ግን እንዲያጠምቅ ከእግዚአብሔር የተላከ ሰው ነበር። እኔ ግን የተጠመቀ አይመስለኝም። ምክንያቱም ሰዎች አንተ ክርስቶስ ካልሆነህ ለምን ታጠምቃለህ ሲሉት እኔ ለንስሃ ነው ማጠምቀው እውነተኛ አጥማቂ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ሚያጠምቀው እየመጣ ነው ብሎ ነው የመለሰላቸው። መንገድ እንዲያዘጋጅ አጥማቂ ሆኖ የተላከ የመጀመሪያው ሰው እንደሆነ ነው ማስበው
Sep 15, 2021Read bible sweety
Sep 15, 2021wef እርሱ አጥማቂ እንጂ ተጠማቂ አይደለም! ደግሞ ማንም አላጠመቀውም፤ እርሱ ነው የመጀመሪያው አጥማቂ!
Sep 15, 2021Eshi amsgnalew
Sep 15, 2021