ሰላማቹ ይብዛ! ስለሳይነስ የምታውቁትን አካፍሉኝ ምልክቶቹን መፍትሄውን አጠቃላይ ዘርዘር ያለ ነገር እባካቹ እህቴ ታማብኝ ነው መፍቴ እሻለው!
Sep 12, 2021ሳይነስ መንስኤው እና መከላከያው አንዳንድ ሰዎች የሳይነስ እና የሳይኖሳተስን ልዩነት ሳይገነዘቡ ሳይነስ አለብኝ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ሳይነስ ሁሉም ሰዎች አላቸው፡፡ይሁን እንጂ የሳይነስ ክፍሎቹ ለበሽታ ሲጋለጡ ሳይኖሳተስ ይባላል፡፡ ሳይነሶች የሚባሉት በፊታችን አጥንት ስር የሚገኙ ትናንሽ ክፍት ቦታዎች ሲሆኑ በግንባራችን፣በጉንጫችን፣በአፍንጫችን ውስጥ እና ከአንጎላችን በታች ያሉ ንፁህ እና በአየር የተሞሉ ሳጥኖች ናቸው፡፡ አራት የሳይነስ ዓይነቶች አሉ፡፡ 1. ማክስለሪ ሳይነስ - ከልደት ጀምሮ ከሰው ልጅ አካላዊ እድገት ጋር አብሮ የሚያድግ ነው፡፡ይህ የሳይነስ አይነት ከላይኛው የጥርሳችን አካል ማለትም ከመንጋጋችን ጋር ይያያዛል፡፡በመሆኑም የጥርስ ህመም ባለባቸው ሰዎች ላይ በሽታው በቀላሉ ወደ ሳይነስ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 2. ፍሮንታል ሳይነስ - የምንለው ደግሞ ከግንባራችን ስር የሚገኝ ነው፡፡ከዚህ ሳይነስ ጀርባ አንጎላችን የሚገኝ ሲሆን ሳይነሱ ከአንጎላችን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አለው፡፡ ስለዚህ የፍሮንታል ሳይነስ ለህመም ከተጋለጠ አንጎላችንን ለበሽታ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ 3. ኤትሞይዳል ሳይነስ - የምንለው መገኛው ከአይናችን ክፍል ጋር ሲሆን የአይናችን ግድግዳ ከኤትሞይዳል ሳይነስ ግድግዳ ጋር ይገናኛል፡፡በመሆኑም የኤትሞይዳል ሳይነስ በበሽታ ከተጠቃ በሽታው በቀጥታ አይናችንን ወይንም አንጎላችንን በቀላሉ ያጠቃል፡፡ 4. ስፔኖዳል ሳይነስ - የሚባለው ከልደት ጀምሮ አይኖርም፡፡ነገር ግን ከስምንት ዓመት ጀምሮ ማደግ የሚጀምር የሳይነስ ዓይነት ነው፡፡ይህ ሳይነስ ለአንጎላችን በብዙ አቅጣጫ በጣም ቅርብ ነው፡፡ይህ ሳይነስ በበሽታ ከተጎዳ ለማጅራት ገትር በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ የሳይነስ ጥቅሞች ፡- o ድምፃችን ጥርት ብሎ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡ o እነዚህ ሳጥኖች ክፍት ወይንም ባዶ ስለሆኑ የራስ ቅላችንን ክብደት ይቀንሳሉ፡፡ o የፊት ቅርፃችን እንዲስተካከልም ያደርጋሉ፡፡ የሳይኖሳተስ በሽታ መንስኤዎች - በአለርጂ፣በኢንፌክሽን፣በእብጠት፣ እጢ እና በአደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡ የሳይኖሳተስ በሽታ ምልክቶች - አፍንጫ በፈሳሽ መታፈን፣የራስ ህመም፣ወፍራም እና ቢጫ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ እንዲሁም ማስነጠስ የመሳሰሉ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡ የሳይኖሳተስ በሽታ በሚከሰት ጊዜ የሳይነሳችን ክፍሎች ፈሳሹን የሚያስወግዱበት ጥቃቅን ቱቦ በመጥበብ መወገድ ያለበት ፈሳሽ እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡በዚህ ጊዜ በእያንዳንዱ የሳይነስ ክፍላችን ላይ ያሉት ቆሻሻ አስወጋጅ አካላት ስራቸውን ባግባቡ መስራት አይችሉም፡፡ መከላከያ መንገዱ ፡- የሳይኖሳተስ በሽታ መንስኤዎች የሆኑትን አለርጂ፣ኢንፌክሽን፣እብጠት፣እጢ እና የተለያዩ አደጋዎች ሳይነሶቻችንን እንዳይጋልጡ አስቀድመን መከላከል እና እራስን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም ራስን ከአቧራ ማራቅ፣ቅዝቃዜን መከላከል እና አካልን በተቻለ መጠን ማሞቅ ያስፈልጋል፡፡ ሽቶን ጨምሮ ለሳይኖሳተስ የሚያጋልጡ ሌሎች ሽታዎችን ማስወገድ ያስፈልጋል።
Sep 12, 2021