ፍቅር ከጀመርን 7ወር ይሆነናል እና አሁን ጥሩ ፍቅር ውስጥ ነን። ነገር ግን ሁለታችን በሃይማኖት ሰለማንገናኝ በኛም ማህበረሰብ ያልተለመደ ስለሆነ ስለወደፊቱ ስናቅድ በተለይ ስለቤተሰቦቻችን ስናስብ እስከትዳር መቀጠላችን በጣም ያሰጋናል። ምን ይሻለናል?.. ንገሩኝ🙏
Sep 09, 2021እኔ በአንድ ነገር አምናለው። እሱም በሀይማኖት ወይም በእምነት! በእምነታችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን እንማራለን። የእኛነታችን ትርጉምም የምናገኘው በእምነታችን በኩል ነው። እያንዳንዱ እምነት የተለያየ ቢሆንም አንድ ነገር ያስተሳስራቸዋል። እሱም እያንዳንዱ የራሱ አምላክ አለው። በክርስቲያኑ እግዚአብሔር ፣ በሙስሊሙ አላህ። ስለዚህ የእነዚህ እምነት ተከታዮች ኑሮዋቸው ሁሉ የሚያምኑትን አምላክ ለማስደሰት ያውላሉ። ታዲያ ሁለት የተለያየ እምነት ካላችሁ የምታመልኩት አምላክ በዚህ ደስ ይለዋል? ትዳሩስ ምን ዓይነት ይሆን? ልጆች ሲወለዱስ? ወደአንድ እምነት መምጣት ከቻላችሁ እሰየው! ካልሆነ ግን ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል። የፍቅር ጓደኛን ከአምላክ ጋር ማወዳደር ይመስለኛል። ዋናው ጉዳይ ማህበረሰቡ ምን እንደሚያስብ አይደለም። ዋናው ጉዳይ በግንኙነታችሁ ፈጣሪ ደስተኛ ነው ወይ? ነው መሆን ያለበት። በዚህች ምድር ለጥቂት ጊዜ ነው የምንኖረው። ከዛ የማይቀረው ሞት ይመጣል፤ በአምላካችንም ፊት የምንጠየቅበት ጊዜ ይመጣል። በዚህ ምድር ለምንኖርባት ትንሽ ጊዜ ብለን አንድን ነገር ብንመርጥና ወደፊት ግን ቅጣት ቢጠብቀን ምንድን ነው ትርፉ? ይህ የሕይወት ጉዳይ ነውና ቆም ተብሎ ሊታሰብበት ይገባል። በግሌ የተለያየ ሀይማኖት ኖሯቸው የተጋቡ ባልና ሚስት አውቃለው። ግን ትዳራቸው ቀላል የሚባል አይደለም። ፈጣሪ ወይስ ፍቅረኛ? ምርጫውን ለእናንተ እተዋለው።
Sep 10, 2021