ስሙኝ እስቲማ እንደምን አላችሁ አንድ የምጠይቀው ነገር ነበረኝ እሱም ምንድነው በቤተክርስቲያናችን ምሥጢር የተባለ :የተሸሸገ ድብቅ ስውር .. ማለት ነው እነዚህም ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት በእምነቱ ላሉ ማወቅ ለሚገባቸው ለምዕመን ሊሆን ይችላል ለሌላው በቅደም ተከተል መጀመሪያ ያለጥርጥር አምኖ ተቀብሎ ለሚተገብረው ሰው የሚሰጥ ነው ግን አሁን አሁን በዩቲዩብ በሌላም በቴለቪዥን መስኮትም እየተሰጠ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሀሳቡ ጥሩ ነው ግን ምሥጢር ተብሎ እንዲህ መውጣቱን እንዴት ታዩታላቹ
Sep 08, 2021ምሥጢር ማለት በሥጋ የሚፈጽም ግን ያልተገለጠ መንፈሣዊ ትግባር ለማለት እንጂ የማይነገር ለማለት አይደለም። ምስጢረ ጥምቀት ሲል እኛ የምናየው በውሃ መረጨትን ወይን መነከርን ነው፥ ግን ነፍስ ሲያድስ የሥላሴ ልጅነትን ሲያስገኝ በዓይነሥጋ የሚታይ ነገር ባለመሆኑ ምስጢር ይባላል።
Sep 08, 2021